Active Projects

የስብከት ኬላ አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት

ማኅበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ የሐዋርያዊ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውጭ ያሉ ወገኖችን በማስተማርና በማሳመን በርካታ ወገኖችን በማስጠመቅ የቤተ ክርስቲያን አባላት እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናትና አዳራሽ የሌላቸው በመሆኑ አዳዲስ አማንያኑ የሚማሩት በዛፍ ሥር ወይም በአንዳንድ ወገኖች ቤት ውስጥ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ያሉ  በርካታ ወገኖች ለመማር እና የሥላሴ ልጅነትን ለማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ [give_form id="12229" show_title="true" show_goal="true" show_content="above" display_style="onpage"]

የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች

ሥራህን ሥራ (በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ)

ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነዉ። ቢቻለዉ እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ። በእርግጥ ሥራዉን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን ኦንዲጠይቁህ እጅግ ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ፥ሄሮድስ፥ሀናንያ፥ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በፀና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኽኝን ስራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።

አባ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፩፱፫፪፡፩፱፰፪ ዓ.ም.

Abune Gorgorios Kale'i