ለአብነት ትምህርት ቤቶችና መንፈሳዊ ኮሌጆች ስልጠና

ለአብነት ትምህርት ቤቶችና መንፈሳዊ ኮሌጆች ስልጠና

$0 of $59,500 raised

የስልጠናው አስፈላጊነት፡-

 • የቤተክርስቲያናችን የአብነት መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም የነገረ መለኮት ተማሪዎች አስፈላጊውን የቤተክርስቲያን ትምህርት በመማር ምዕመናንን ከተኩላዎች መጠበቅ ይችሉ ዘንድ፣
 • በቀጣይ ለቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎት የዘመኑን ነባራዊ ሁኔታ የተረዱና ከዓለማዊነት /ግሎባላይዜሽን/ ተፅዕኖ የጸዱ ተተኪዎችን ማፍራት እንዲቻል፣
 • የአብነት መምህራን፣ ተማሪዎችና ደቀመዛሙርት የቤተክርስቲያኒቱ ሀብት የሆኑ ምዕመናንንና ያሏትን ሀብትና ንብረቶች በአግባቡ መምራትና ማስተዳደር እንዲችሉ፣ የማስተማር፤ የመምከር፤ ምእመናንን የመጠበቅ አገልግሎቶችን በትጋት እንዲያከናውኑ ለማበረታታት
 • ሰልጣኞች በቤተክርስቲያን ያሉትን ነባራዊ ችግሮች በማወቅ አስፈላጊውን የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ለማስቻል
 • ሰልጣኝ የአብነት መምህራን፣ ተማሪዎች እና ደቀመዛሙርት በወረዳዎች እና በአጥቢያቸው ያሉትን ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ተግዳሮቶችን በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲቀይሱ ለማስቻል
 • ሰልጣኞች በጠረፋማ እና አህዛብና መናፍቃን በሚበዙባቸው አካባቢዎች ተዛውረው በማስተማር ኢ-አማንያንን በማሳመን፣ ከእምነታቸው ወጥተው የነበሩትን ደግሞ አስተምረው በመመለስ በጥምቀት የቤተክርስቲያን ልጅነትን እንዲያገኙ የመምህርነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል
 • አብነት ተማሪዎች ያላቸውን የአስተዳደር ክህሎት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በመቀመር ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት የመፍትሄ አካላት እንዲሆኑ ማብቃት ነው፡፡

የስልጠናው ዓላማ፡-

 • በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአብነት መምህራን፣ ተማሪዎችና ደቀመዛሙርት ከተማሩት የቤተክርስቲያን ትምህርት በተጨማሪ የቤተክርስቲያንን አስተምሮዋን ጠንቅቀው እንዲረዱና በየሄዱበት ቦታ ሁሉ ህዝበ ክርስቲያኑን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ምስጢራትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እና ሌሎችንም በማስተማር የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ እንዲረዱና እምነታቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ነው፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች፡-

 • የምስክርና መጋቢ አብነት ትምህርት ቤቶች መምህራንና ካህናት
 • በገዳማት የሚገኙ አባቶች መነኮሳት
 • በምስክር ፣በመጋቢ ፣በአዳሪ ት/ቤቶች እንዲሁም በየአጥቢያዎች በመማር ላይ ያሉ አብነት ተማሪዎች
 • ከጠረፋማ አካባቢዎች ፣መናፍቃንና አህዛብ ከሚበዙባቸው አህጉረ ስብከት የተመለመሉና መሠረታዊ የአብነት እውቀት ያላቸው
 • በመንፈሳዊ ኮሌጆች ለሚማሩ የነገረ መለኮት ደቀመዛሙርት ናቸው፡፡

አጠቃላይ የስልጠናው ተሳታፊዎች ብዛት 2025 ሲሆን ዝርዝሩ ከታች በተገለጸው ሰንጠረዥ ተገልጿል፡፡

ተ.ቁ  ለደረጃ አንድ ለደረጃ ሁለት ለደረጃ ሦስት ለመንፈሳዊ ኮሌጅ 
የሰልጣኞች ብዛት የመ/ራን ብዛት የሰልጣኞች ብዛት የመ/ራን ብዛት የሰልጣኞች ብዛት የመ/ራን ብዛት የሰልጣኞች ብዛት የመ/ራን ብዛት
1385 72 360 32 140 20 140 6

ጠቅላላ ለስልጠናው የሚያስፈልግ በጀት፡- ደረጃ 1– ብር 1‚125‚945

ደረጃ 2– ብር 376‚260 እና

ደረጃ 3– ብር 165‚960 ሲሆን

ጠቅላላ የበጀት ፍላጎት ድምር፡-   ብር 1‚668‚165 (~$59,500)ይሆናል፡፡

$
 
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50 One Time