ድረሱልንና አብረን መንግስቱን እንውረስ

ድረሱልንና አብረን መንግስቱን እንውረስ

$1,720 of $5,333 raised

በማኅበረ ቅዱሳን የዲሲ ንዑስ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ክፍል እና ቀሲስ ምዕራፍ ፀጋዬ ከሚያስተምራቸው የመንፈስ ልጆቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ በገጠርና ጠረፋማ አከባቢ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ።

“በወንጌልም ማኅበርተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ቆሮ 9፡23
መግቢያ

የሐዋርያዊ አገልግሎት ውሱንነት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሚናፍቁ በገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች መድረስ እንዳይቻል አድርጎታል፡፡ ይህም መናፍቃኑ ቀድመው በመግባት ብዙዎችን ወደ ምንፍቅና እንዲወስዷቸው በር ከፍቶላቸዋል፡፡ብዙ ወገኖች እውነተኛውን የወንጌል ብርሃን ሳይመለከቱ በእግዚአብሔር ቃል ሳይጸኑ ፣ በገጠር በጠረፋማው የሀገራችንና በአጠቃላይ የዓለማችን ክፍል ተበትነው ፣ ድኅነትን እንደናፈቁ ፣ በጎውን ነገር ሳያዩ ሞተ ሥጋ ይቀድማቸዋል፡፡

የሐዋርያዊ አገልግሎት ውሱንነት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚታይባቸው አካባቢዎች መካከል የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት አንዱ ሲሆን በዚህ ሀገረ ስብከት የሚገኙ ወገኖችን መልካሙን መንገድ የሚያሳያቸው አጥተው ወደ ሌሎቸ የእምነት ቤቶች የሚሄዱትን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለማምጣት፣ አስተምሮ ለማስጠመቅ እና የሥላሴን ልጅነት ያገኙትን ምዕመናን የቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት አግኝተው በምግባር በሃይማኖት እንዲጸኑ ለማድረግ አዳዲስ አማንያን ባሉበት የቅድስት ቤተክርስቲያንን አገልግሎት እንዲያገኙ ከተጠማቂያን መካከል ጭምር በብዛት እና በጥራት የሚያገለግሉ የቅድስት ቤተክርስቲያን አገልጋይ ማፍራትና ለአዳዲስ አማንያን መገልገያ የሚሆኑ አብያተ ክርስቲናትን ማነጽ ይጠበቃል፡፡

በከምባ ወረዳ ሐሪንጋ አካባቢው ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ከምባ ወረዳ ከሚገኙት 30 ቀበሌዎች መካከል 14 ቀበሌዎች ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት ሲገኙ በቀሪ 16 ቀበሌዎች የሐሪንጋን ቀበሌ ጨምሮ መገልገያ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናትና አገልጋይ ዲያቆናትና ካህናት የሉም፡፡

ምንም እንኳ አብዛኛው ማኅበረሰብ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ ወገኖች በርካታ ናቸው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከወረዳው የተወሰኑ ወጣቶችን በመመልመል ሰባክያነ ወንጌልነት አሰልጥኖ አሰማርቷል፡፡

በዚህ ቀበሌ ግን የሚያገለግል ሰባኬ ወንጌል የለም፡፡

በአካባቢው ከግቢ ጉባ ወጥተው ለሥራ የተሰማሩ አገልጋዮችና ከሌላ ቦታ የሚገኙ ሰባክያን በፈጸሙት አገልግሎት በ2012 ዓ/ም ብቻ 600 አዳዲስ አማንያን ተጠምቀዋል፡፡

በከምባ ወረዳ እና አካባቢው ወደፊት መተግበር ያለባቸው ዓበይት ተግባራት

በወረዳው ያለውን የሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናክሮ በመቀጠል በርካታ ወገኖችን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማምጣት ይጠበቃል፡፡ለዚህም የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡ከእነዚህም መካከል

በአካባቢው የሐዋርያዊ አገልግሎቱን ተደራሽና ውጤታማ የሚያደርጉ ሰባክያነ ወንጌል ማሰልጠንና ማሰማራት

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ለሚማሩ ወገኖች መማሪያ የስብከት ኬላ አዳራሾችን መሥራት

ተምረው አምነው ለተጠመቁ አዳዲስ ምእመናን ሥርዓተ አምልኳቸውንና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጽሙበት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መገንባትና አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50