የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እና መጠነኛ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ

የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እና መጠነኛ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ

$44,070 of $100,000 raised

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና በልጆቿ ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ እና ምእመናንን በግፍ እየተገደሉ ይገኛሉ፡፡ በቅርብ ጊዜ በተከሰተው ጥቃትም ብዙ ንብረት ወድሟል የሰው ህይወትም ጠፍቷል እንደ ማሳያ፦
 በ10 የኦሮምያ ክልል ዞኖች እና 2 የከተማ አስተዳደር 67 ክርስቲያኖች በግፍ ተገለዋል ከሟቾች ውስጥም አንዱ ካህን ናቸው፡፡
 በየቦታው አሉ የሚባሉ ኦርቶዶክሳውያን በድጋሚ ላያንሰራሩ ሆነው ንብረታቸው የወደመ ሲሆን የወደሙ ንብረቶች በአብዛኛው ኢንተርናሽናል ሆቴሎች፤ ሌሎች ሆቴሎች፤ መኖሪያ ቤቶች፤ ትምህርት ቤቶች፤ ካፌዎች ፤ ምግብ ቤቶች፤ ግሮሶሪዎች ፤ማከፋፈያ ሱቆች/የሸቀጣሸቀጥ፤ የእህል ቤቶች፤ የቤትና የስራ መኪኖች (ከአንድ ቤት እስከ 6 መኪና ድረስ)፤ የኮንስትራክሽን እንዲሁም የትራንስፖርት መኪኖች ፤ባጃጅ ፤ሞተር ሳይክል፤ ታሪካዊ ቅርሶች እና የመሣሠሉት ይገኙበታል፡፡
 በገጠር አካባቢ በማሣ ላይ ያሉ ሰብሎችም እንዲወድሙ ተደርጓል፡፡
 በአሁኑ ወቅት ከ7,000 የማያንሱ የጥቃት ሰለባዎች በቤተክርስቲያና በአንዳንድ መጠለያዎች ተጠልለው ድጋፍ እየጠበቁ ይገኛል፡፡
 አንድ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል፡፡

ስለሆነም አሁን ላለው አስቸኳይ ችግር መድረስ ይገባል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ጊዜያዊ እርዳታ እና መጠነኛ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ ለማድረግ በሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት አስተባባሪነት የተጀመረው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑ ክርስቲያኖች በአንድነትና በትብብር ብንቆም ያለንን አቅም ያሳየንበት ነው ማለት ይቻላል:: መላው የማኅበሩ አባላት በዚህ በማኅበረ ካህናቱ እየተደረገ ባለው የገቢ ማሰባሰብ ጥረት እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን እየተሳተፍን መሆኑ ይታወቃል:: ነገር ግን እንደ ማኅበር አጋርነታችን የበለጠ ለማሳየት እስከ አንድ ሳምንት ከማኅበሩ አባላት በማሰባሰብ እንደ ማኅበር በተጨማሪነት በመለገስ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማበረታታት የአሜሪካ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚው ወስኗል፡፡ በመሆኑም ምንም እንኳን በተለያየ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ስትሳተፉ የቆያችሁ እንደሆነ ብናውቅም ሳትጨነቁ አቅማችሁ የፈቀደውን ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ድጋፍ እንድታደርጉና አጋርነታችን እንድናሳይ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የሰማእታቱ በረከት ይደርብን!!

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $20