የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርት እድል ፕሮጀክት

0 Template form (enter title here)

$400 of $75,539 raised

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ማእከል ሆና ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚያስፈልጋትን የሰው ሀይል በእውቀት መግባ በስነ ምግባር ኮትኩታና አሳድጋ አበርክታለች፡፡ በዚህም ለቤተ ክህነት እና ቤተ መንግሥት ከአገልጋይ ካህናት እስከ ቅዱሳን ነገሥታት ማፍራት ችላለች፡፡ ነገር ግን ይህ አስተዋጽኦ በተለያዩ ጊዜ በተነሱ ስሁት ርዕዮተ ዓለማዊ ፈተናዎች እየተዳከመ የመጣ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ችግሩን ተረድቶ የአብነት ትምህርትና ዘመናዊ (አስኳላ) ትምህርት ተናበው እንዲሔዱ ሁለቱም ለቤተክርስቲያንና ለሀገር የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ በሁለት በኩል የተሳሉ አገልጋዮች እንዲፈሩ ለማድረግ በታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ (ዳግማዊ ቄርሎስ) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተሰየመ ነጻ የትምህርት እድል (scholarship) መርሐ ግብር ቀርጾ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በማድረግ ልዩ ልዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ እና ተጨባጭ ለውጦች ማምጣት ተችሏል፡፡ በዚህ መሠረትም ከዘመናዊ ወደ አብነት ትምህርት ቤት የሚገቡ የነጻ የትምህርት እድሉ ተጠቃሚዎች በተመረጡ ጉባኤ ቤቶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚደረግ ሲሆን ከአብነት ወደ ዘመናዊ እንዲሁም በመንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲማሩ እድሉ የተሰጣቸው መምህራንና ደቀመዛሙርት በተመደቡበት የትምህርት ተቋም ወጪያቸውን በመሸፍን እንዲማሩ ይደረጋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

 • በትውልዱ መካከል የተከፈተውን ክፍተት (ከ1960 ዎቹ በኋላ ከቤተመንግስትና ቤተ ክህነት መለያየት በኋላ) ይሞላል ድልድይ ሆኖ ያገናኛል፤
 • ለቤተ ክርስቲያን ተተኪ መሪዎችን ከማፍራት አንጻር አስተዋጽኦው የጎላ ነው፡፡
 • ዓለም አቀፍ አገልግሎት እና ሐዋርያዊ ተልእኮ ከመፈጸም አንጻር የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
 • የአብነት ትምህርትን በትውልዱ ከማስፋፋትና ተወዳጅ ከማድረግ አንጻር ጠቀሜታው ሰፊ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

ሁለንተናዊ አቅምና ዝግጁነት ያላቸው በስነ ምግባር የታነጹ አገልጋዮችንና መሪዎችን ለቤተክርስቲያን ብሎም ለሀገራችን ማፍራት፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

ለአዳዲስ አማንያን መገልገያ የሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት ግንባታ

0 Template form (enter title here)

$2,550 of $240,385 raised

አስፈላጊነት፡- ተምረው አምነው የተጠመቁ አዳዲስ አማንያን ቤተ ክርስቲያን በአቅራቢያቸው ስለሌለ አዳዲስ አማንያን በዳሰሳ ጎጆ በመሰባሰብ በተከታታይ ቃለ እግዚአብሔር ይማራሉ፣ አምላካቸውንም ያመሰግናሉ፡፡ ሥርዓተ ጥምቀታቸውን ለማስፈጸም ከብዙ ርቀት ማጓጓዝ አልያም በድንኳን ቅዳሴ መፈጸም ይጠበቃል፡፡

 ዓላማ፡ አዳዲስ አማንያን  የሚማሩበት ፣ የሚያስቀድሱበት ፣ ልጆቻቸውን ክርስትና የሚያስነሡበትና በአጠቃላይ ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጽሙበት  ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት በመገንባት አገልግሎት ላይ ማዋል።

“ቤቱን ሥሩልን፣እኛ እንማርበታለን፤ ልጆቻችንም ይውሉበታል፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ያድርባቸዋል፡፡በዚህም ጥሩ ሰው ይሆናሉ፡፡”   ከዳሰነች ምእመናን መካከል

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የስብከት ኬላ (መካነ ስብከት) አዳራሽ ሥራ

0 Template form (enter title here)

$1,756 of $76,924 raised

አስፈላጊነት፡- ማኅበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ የሐዋርያዊ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውጭ ያሉ ወገኖችን በማስተማርና በማሳመን በርካታ ወገኖችን በማስጠመቅ የቤተ ክርስቲያን አባላት እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናትና አዳራሽ የሌላቸው በመሆኑ አዳዲስ አማንያኑ የሚማሩት በዛፍ ሥር ወይም በአንዳንድ ወገኖች ቤት ውስጥ ነው፡፡

ዓላማ፡- ሕንጻ ቤተክርስቲያን በሌሉባቸው አካባቢዎች አዳዲስ አማንያንን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት   እንዲያገኙ ትምህርተ ኃይማኖት የሚማሩበት የሚሰባሰቡበት፣ የሚጸልዩበትና እርስ በእርስ የሚመካከሩበት 5 የስብከት ኬላ አዳራሾችን መስራትና ለአገልግሎት ማብቃት ነው፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

ለአዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት ማስፈጸሚያ (ክርስትና ማስነሽያ)

0 Template form (enter title here)

$3,260 of $288,462 raised

አስፈላጊነት፡ ከትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዐበይት ተግባራት መካከል አዳዲስ አማንያን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት በመስጠት እንድያምኑና እንዲጠመቁ ማደረግ ይገኝበታል::

 ላማ፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖት ተምረው ላመኑ 50,000 አዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት በመፈጸም የቤተ-ክርስቲያን አባላት ለማድረግ የክርስትና ማንሽያ ነጠላ፣የአንገት ማተብና መስቀል ማሟላት፣ መስተንግዶ እና ትራንስፖርት በማቅረብ ሥርዓተ ጥምቀቱን መፈጸም።

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤት ማቋቋሚያ ፕሮጀክት

ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤት ማቋቋሚያ ፕሮጀክት

$990 of $120,908 raised

በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ይህ የፕሮጀክት ጥናት መረጃ እስከተወሰደበት ጊዜ ድረስ በ18 ወረዳ ቤተክህነቶች የተዋቀረና በአጠቃላይ 382 የሚደርሱ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ ከአሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል 55 (14 በመቶ) ምንም አገልጋይ የሌላቸውና አገልግሎትም የማይሰጥባቸው ሲሆን፤ አገልጋይ ያልተሟላላቸውና በከፊል አገልግሎት የሚሰጥባቸው ደግሞ 300 (78.5 በመቶ) ናቸው፡፡ የተሟላ ቀሳዉስትና ዲያቆናት ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት 27 ናቸዉ፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት፡

 • የቤተክርስቲያን ተረካቢ የሚሆኑ የአካባቢውን ልጆች በማስተማር ቀሳውስት እና ዲያቆናትን በሚፈለገው መጠን ለማፍራት፤
 • የአብነት ትምህርት ቤቱ በየሁለት ዓመቱ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር በሀገረ ስብከቱ በአገልጋይ እጦት ምክንያት የተጓደለውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጠናከር እና የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ ማድረግ
 • ለምዕመናኑ በቂ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት፤ በቋንቋቸው ወንጌል በማስተማር ያመኑትን በሃይማኖታቸው ፀንተው እንዲቆዩ ለማድረግና የጠፉትን ለመመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ፡

በሀገረ ስብከቱ አዲስ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ በማካሄድ ቀሳውስት እና ዲያቆናት በማፍራት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ እና የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ይዘት፡

የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የአብነት ት/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት በውስጡ የሚይዘው

 • ለ40 ተማሪዎች ማደሪያ የሚያገለግል ባለ አምስት ክፍል አንድ ቤት
 • 40 ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል አንድ ጉባዔ ቤት
 • ለ40 ተማሪዎች የሚያገለግል ባለ ስድሰት ክፍል አንድ መፀዳጃ ቤት

ለአብነት ት/ቤቱ የምግብ ማብስያና ዕቃ ማስቀመጫ የሚያገለግል ባለሁለት ክፍል አንድ ቤት።

 

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምህረት የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት

የጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምህረት የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት

$19,844 of $307,000 raised

. የፕሮጀክቱ አጠቃላይ መረጃ

 • የፕሮጀክቱ ስም፡– ጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐብየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ መርቆሪዎስ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት
 • ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት /ስብከት፡ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት
 • ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡– ሐምሌ 25/ 2014 ዓ.ም
 • ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡- ነሐሴ 30/ 2015 ዓ.ም
 • የፕሮጀክቱ አጠቃላይ በጀት፡ 16,000,250.31 (አስራ ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ከ 31 ሳንቲም)
 • የፕሮጀክቱ አፈጻጸም፡ 10%
 • የፕሮጀክቱ ድጋፍ አድራጊ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ በጎ አድራጊ ምእመናን ድጋፍ አድራጊነት የሚተገበር ፕሮጀክት ነው፡

. የፕሮጀክቱ አጭር መግለጫ

ከጎንደር ከተማ ታሪክ ጋር የተያያዘዉ የደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምህረት ወቅዱስ መርቆሪዎስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በፈጻሜ መንግሥት በአጼ ተክለጊዮርጊስ (ከ1772 እስከ 1777 ዓ.ም) ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ሲሆን ተካዩ በወቅቱ የኢትዮጲያ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት የሰሜኑ ገዥ ራስ ቢትወደድ ገብሬ ናቸዉ፡፡ ከአቃቤ ሰዓት ከብቴ አራቱን ጉባኤያት የተማሩት ሊቅ መምህር ወልደ አብ የደብሯን አለቃነት ደርበው በማስተዳደር የመጽሕፍተ ብሉያት ጉባኤ ቤት በ1773 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡ መምህር ወልደ አብም ለደብሩ የመደቡትን የብሉያትን ጉባኤ መደበኛ አድርገው ሌሎችንም ሦስቱን ማለትም ሐዲሳትን ሊቃውንትን እና መነኮሳትን በመጨመር በርካታ ሊቃውንትን አፍርተዋል፡፡ ከመምህር ወልደ አብ ጀምሮ እስካሁን ድረስ 16 መምህራን በጉባኤ ቤቱ ወንበር ዘርግተው የአስተማሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት መምህር ፍሬሕይወት አራጌ ከ60 በላይ ደቀመዛሙርትን እያስተማሩ ይገኛሉ።

ጉባኤ ቤቱ ከዚህ በላይ ተቀብሎ መስተማር የሚጠበቅበት ቢሆንም የተማሪዎች እና የመምህራን መኖሪያ ቤት፤ የጉባኤ (መማሪያ) ቤት፤ የቤተ መጻሕፍትና የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ቦታ ችግር ስላለበት በሚፈለገው መጠን ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ አልቻለም፡፡ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን የጉባኤ ቤቱን ችግሮች ለመፍታት ይህን ፕሮጀክት ቀርጾ መተግበር አስፈላጊ ሆኗል።

. የፕሮጀክቱ ግብ

ዘመኑን የዋጀ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን በማፍራት የቤተክርስቲያን አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ፡፡

 

. የፕሮጀክቱ ዓላማ

 • በአብነት ት/ቤቱ ያለውን የማደሪያ ቤት፣ የጉባኤ ቤት፣ የቤተ መጻሕፍት እና የሥልጠና ቦታ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ባለ 2 ወለል ሕንጻ መገንባት፡
 • ከትምህርቱ ጎን ለጎን ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች በመስጠት በሁለተናዊ መልኩ ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ።

. በፕሮጀክቱ የደረሰበት ደረጃ)

በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ግንባታ 15% የደረሰ ሲሆን የመሠረት ሥራዎች ተጠናቀው የግራውንድ ኮለን በመሠራት ላይ ይገኛል፡፡

 

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ ሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና

የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ ሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና

$100 of $96,154 raised

የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ ሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና

የሥልጠናው አስፈላጊነት፡-

 • በተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የሰባክያነ ወንጌል እጥረት ችግር በመቅረፍ ቅዱስ ወንጌል ተደራሽ ለማድረግ ይረዳል፡፡
 • የመምህራኑን አቅም የሚያጎለብትና ለተሻለ አገልግሎት የሚያበቃ ይሆናል፡፡
 • በአካባቢው ለሚኖሩና አዲስ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት በማስተማር ምእመናኑ በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ያደርጋቸዋል፡፡
 • የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ላልደረሳቸው ወገኖች የቤተ ክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት በማስተማር አሳምኖ ለማስጠመቅ ይረዳል፡፡

የሥልጠናው ዓላማ፡ በተለያዩ ገጠራማና ጠረፋማ አካባቢዎች የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ አዳዲስ አማንያንን ለማስተማርና ለማስጠመቅ፣ ምእመናንን በምግባር በሃይማኖት ለማጽናትና የጠፉትን ለመመለስ የሚያገልግሉ 1000 ሰባክያነ ወንጌል ማሰልጠን።

“ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? (ሮሜ ፲፡፲፬)

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50