የስብከት ኬላ አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት

የስብከት ኬላ አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት

$10,095 of $200,000 raised

ምእመናን አፈር ላይ ተቀምጠው በመዝሙር አምላካቸውንም ሲያመሰግኑ

የፕሮጀክቱ አስፈላነት

ማኅበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ የሐዋርያዊ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውጭ ያሉ ወገኖችን በማስተማርና በማሳመን በርካታ ወገኖችን በማስጠመቅ የቤተ ክርስቲያን አባላት እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናትና አዳራሽ የሌላቸው በመሆኑ አዳዲስ አማንያኑ የሚማሩት በዛፍ ሥር ወይም በአንዳንድ ወገኖች ቤት ውስጥ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ያሉ  በርካታ ወገኖች ለመማር እና የሥላሴ ልጅነትን ለማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ ይህን የሐዋርያዊ  አገልግሎት በማጠናከር  ወንጌል ተምረው የሚጠመቁ  አዳዲስ አማንያንን  ቁጥር መጨመር ያስፈልጋል፡፡  ለዚህ ደግሞ እነዚህ ወገኖች ስብከተ ወንጌል የሚማሩበት፤ በመዝሙር

እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት፣ ሕጻናትና ወጣቶች በሰንበት ት/ቤት ታቅፈው የሚማሩበት እና የአዳዲስ አማንያንን ሥርዓተ ጥምቀት ለመፈጸም የሚያስችል የስብከት ኬላዎችን (መካነ ስብከት) አዳራሽ መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ  የሰባኬ ወንጌል እጥረትና ሰዎችም ተበታትነው ስለሚኖሩ በአጭር ጊዜ ተደራሽ ማድረግ ስለማይቻል ይህ አዳራሽ ከተገነባ በአንድ ቦታ ብዙ ሰዎችን ማስተማር ይቻላል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

ሕንጻ ቤተክርስቲያን በሌሉባቸው አካባቢዎች አዳዲስ አማንያንን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት   እንዲያገኙ ትምህርተ ኃይማኖት የሚማሩበት          የሚሰባሰቡበት፣ የሚጸልዩበትና እርስ በእርስ የሚመካከሩበት በተለየዩ አህጉረ ስብከቶች 20 የስብከት ኬላ አዳራሾችን መስራት ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ወጪ

 • ለአንድ ስብከት ኬላ አዳራሽ ሥራ 200,000.00
 • ለ40 ስብከት ኬላ አዳራሽ ሥራ 8,000,000.00

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የአፋን አሮሞ ትርጉም መጻሕፍት ሕትመት ፕሮጀክት

የአፋን አሮሞ ትርጉም መጻሕፍት ሕትመት ፕሮጀክት

$500 of $26,125 raised

መግቢያ

ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ በተነሱባት ፈተናዎች ምክንያት፣“ በጎውን ነገር ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙዎች ቢሆኑም (መዝ 4÷6) በሚፈለገው መጠን በጎውን ነገር እያስተማረች ”ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው”  ማቴ.28÷19 ተብሎ በወንጌል የታዘዘውን ለዓለም ለማዳረስ በምታደርገው አገልግሎት ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች እንቅፋት ሆነውባት አገልግሎቷን በሚፈለገው መጠን መፈጸም እንዳትችል አድርጓታል፡፡

በተለይም በአፋን ኦሮሞ ከተሞችና ገጠራማ አከባቢዎች እጅግ በተጠና መንገድ ኦርቶዶክሳዊነትን ሊንድ በሚችል ሁኔታ በፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ለበስ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ከቀያቸው በማፈናቀል በማሳደድ በመግደል አያሌ አሰቃቂ ጉዳዮች እየተፈጸመ ይገኛል። ምንም እንኳን ራሱን የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አድርጎ የሰየመው አካል አሁን በይቅርታ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ቢመለስም እንደ ዋና መነሻ ሀሳብ አድርጎ የሚያቀርበው የአፋን ኦሮሞ ኦርቶዶክስ ምእመናን በÌንÌቸው የሚያስተምሯቸው ካህናትና በተለይም የትርጉም መጻሕፍት እንደሚያስፈልጎቸው እሙን ነው። ለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በልዩ ልዩ ÌንÌዎች ማስተማር ቅዱሳት መጻሕፍትን መተርጎም ወሳኝ በመሆኑ በአፋን ኦሮሞ ÌንÌ የሚተረጎሙ መጻሕፍትን መርጦ በማሳተም ÌንÌውን ለሚችሉ ምእመናን ማሳየት አስፈላጊ መሆኑ ምንም አያጠራጥርም። ይህንን ተግባር አገልግሎት ለመፈጸም ይህ ፕሮጀክት ተዘጋጅቶል።

ስለዚህ በአፋን ኦሮሞ ክልል መልካሙን መንገድ የሚያሳያቸው አጥተው ወደ ሌሎቸ የእምነት ቤቶች የሚሄዱትን ለመመለስ ፣ አዳዲሶችን አስተምሮ ለማስጠመቅ እና የሥላሴን ልጅነት ያገኙትን ምዕመናን የቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት አግኝተው በቤተ-ክርስቲያን በምግባር በሃይማኖት እንዲጸኑ ለማድረግ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአፋን ኦሮሞ መተርጎም አስፈልጓል። በዚህ መሠረት የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ አንጋልቡ መጽሔትንና የተለያዩ ብሮሸሮችን በማዘጋጀት የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት በመጠቀም ከቤተ ክርስቲያን የኮበለሉትን በማስመለስ፣ አዳዲስ አማንያንን አስተምሮ በማስጠመቅ፣ ያመኑትን በማጽናት በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላነት

በኦሮሚያ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች  የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተደራሽና ውጤታማ በማድረግ  ምዕመናንን በምግባር በሃይማኖት ከማጽናት አንጻር እጅግ ብዙ ክፍተቶች ይታያሉ፡፡በማኅበረሰቡ ቋንቋ በወንጌል አገልግሎት የተሰማሩ አገልጋዮች ቁጥር አናሳ የሆነባቸው፣ ከፍተኛ የካህናት እጥረት የሚታይባቸው፣ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባቸው፣ በከፍተኛ ደረጃ በመናፍቃን የተወረሩ፣ ከፍተኛ የመናፍቃን ተፅዕኖ የሚዳረስባቸው፣ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ከፍተኛ የበጀት፣ የቁሳቁስ ወ.ዘ.ተ ችግሮች በከፍተኛ ደረጃ የሚታዩባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡

በመሆኑም  የአፋን ኦሮሞ ÌንÌ መሰረት ተደርጎ የተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍትን መተርጎምና ማሰራጨት ይበልጥ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን እንዲከታተሉ ያስችላል። በአሁኑ ሰዓት ይህንን ያህል በአፋን ኦሮሞ ÌንÌ ቅዱሳት መጻሕፍት ተተርጉመዋል አያስብልም። ለዚህም በግዕዝም እንዲሁም በአማርኛ ያሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን በአፋን ኦሮሞ ÌንÌ በመተርጎም ይበልጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቱንና ስብከተ ወንጌሉን አገልግሎት ስለሚያግዝ ይህ ፕሮጀክት ተቀርጿል።

የፕሮጀክቱ ዓላማ

ወንጌል ባልተሰስፋፋባቸውና ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች የቅዱስ ወንጌል አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ምእመናንን በምግባር በሃይማኖት ማጽናት፣ የጠፉ ወገኖችን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መመለስ እና አዳዲስ አማንያንን ማፍራት ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዝርዝር ዓላማ

 • በማኅበረሰቡ ቋንቋ ትምህርተ ወንጌልን ተደራሽ ለማድረግ በ3 ርእሰ ጉዳይ የተጻፉ በራሪ ወረቀቶችን 2 ሚሊዮን ኮፒ ማሰራጨት
 • በማኅበረሰቡ ቋንቋ ትምህርተ ወንጌልን ተደራሽ ለማድረግ ቅድሚያ የሚሰጣቸው 3 መጻሕፍትን ትርጉም በማጠናቀቅ በ500ሺህ ኮፒ ማሰራጨት
 • በከተማ ያሉ የማኅበረሰቡ ክፍሎችን ታሳቢ በማድረግ ቅዱስ ወንጌልን ለማድረስ በ6 ከተሞች ወርሐዊ ጉባኤያት ማስጀምርና ማጠናከር

ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው አካባቢዎች

ይህ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አህጉረ ስብከት ይሆናል፡፡ ከእነዚህም መካከል በዋናነት በምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት፣ የምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት፣ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ሰላሌ ሀገረ ስብከት፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ምእራብ አርሲ ዞን ሀገረ ስብከት፣ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ ባሌ ሀገረ ስብከት ፣ ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት፣ ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት፣ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ፣ ምዕራብ፣ ምሥራቅ ጉጂና ቦረና ሀገረ ስብከት፣ ጂማ ሀገረ ስብከትና ኢሉአባቦራ ሀገረ ስብከት ይገኙበታል፡፡

ለፕሮጀክቱ ወጭ

ተቁ

 

ዋና ተግባር

 

መለኪያ

 

ብዛት

 

በጀት
የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ
ቅድሚያ የሚሰጣቸው 3 መጻሕፍት ትርጉም በማጠናቀቅ በ30 ሺህ ኮፒ ማሰራጨት ቁጥር 30000.00 100.00 1,000,000.00
በ3 ርእሰ ጉዳይ የተጻፉ በራሪ ወረቀቶችን 45 ሺ ኮፒ ማሰራጨት ቁጥር 45000.00 1.00     45,000.00
ጠቅላላ ድምር 1,045,000

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ

 • 1,045,000.00 ( አንድ ሚሊየን አርባ አምስት ሺህ ብር )

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የማኅበረሰብ ጎሳ መሪዎች/ሀገር ሽማግሌዎች ሥልጠና ፕሮጀክት

የማኅበረሰብ ጎሳ መሪዎች/ሀገር ሽማግሌዎች ሥልጠና ፕሮጀክት

$500 of $22,500 raised

መግቢያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊት ናት፡፡ አስተምህሮዋና መሠረተ እምነቷ ከአማናዊው መምህር ከኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘ በመሆኑ አማናዊትና ርትዕት ናት፡፡ የዚህች ርትዕት ቤተ-ክርስቲያን ዋነኛ አገልግሎቷም ሐዋርያዊ ተልእኮ ነው፡፡ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታ በአካል የተማሩትን የምስራች ቃል በታዘዙትና በተሰጣቸዉ መንፈሳዊ ኃይል በመታገዝ በብዙ መከራ ዉስጥ ሆነዉ በዓለሙ ሁሉ ዞረዉ አስተምረዋል፤ ነፍሳትንም ለክርስቶስ ማርከዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከቤተክርስቲያን ታሪክ በቀጥታ መረዳት እንደሚቻለው ቤተክርስቲያናችን “ወርቃማ ” ተብለው የሚጠሩ ዘመናትን ያሳለፈች ቢሆንም፣ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጊዜያትንም አሳልፋለች፡፡ ይህም የስብከተ ወንጌል/የሐዋርያዊ አገልግሎት ተደራሽነት እጅግ ውሱን እና የተቋረጠ እንድሆን አድርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሚናፍቁ በገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች መድረስ አልተቻለም፡፡ ይህም መናፍቃኑ ቀድመው በመግባት ብዙዎችን ወደ ምንፍቅና እንዲወስዷቸው በር ከፍቶላቸዋል፡፡ብዙ ወገኖች እውነተኛውን የወንጌል ብርሃን ሳይመለከቱ በእግዚአብሔር ቃል ሳይጠኑ፣ በገጠር በጠረፋማው የሀገራችንና በአጠቃላይ የዓለማችን ክፍል ተበትነው ፣ ድኅነትን እንደናፈቁ ፣ በጎውን ነገር ሳያዩ ሞተ ሥጋ ይቀድማቸዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወገኖችን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለማምጣት አስተምሮ  ማስጠመቅ እና የሥላሴን ልጅነት ያገኙትን ምዕመናን የቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት አግኝተው በምግባር በሃይማኖት  እንዲጸኑ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ለዚህም ከየማኅበረሰቡ ሰባክያነ ወንጌልን ማሰልጠንና ማሰማራት፣ ከማኅበረሰቡ መካከል ተሰሚነት ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች ማሰልጠንና ተልእኮ መስጠት ጥቂቶቹ በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላነት

በገጠራማና ጠረፋማ አካባቢ በሚገኙ አህጉረ ስብከት  የሚገኙ ወገኖች የሥላሴን ልጅነት ሳያገኙ የሚኖሩ ኢ-አማንያን እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ይህም የሆነበት ምክንያት ከማኅበረሰቡ መካከል የሰባኪያነ ወንጌል ባለመኖራቸው ነው፡፡ የመናፍቃኑም እንቅስቃሴም በእጅጉ የሰፋ ነው፡፡

ይህ ቢሆንም አጅግ የሚያስገርመው ነገርና የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ እንድናስተውል የሚያስገነዝበን ያልተጠመቀ ነዋሪ ማኅበረሰብ የአጥምቁንና እኛንም እንደ እናንተ ክርስቲያን አድርጉን የሚለው ጥሪ ነው፡፡ ስለሆነም እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በሁሉም የሀገረ ስብከቱ ወረዳዎች ለሚገኙ ወገኖች የስብከተ ወንጌልን ተደራሽ በማድረግ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት እንዲሆኑ መስራት ይጠበቃል፡፡

ስለዚህ ብዙዎችን ወደ ቤተክርስቲያን ለማምጣት፣ አምነው የተጠመቁትን ደግሞ በምግባር በሃይማኖት ለማጽናት በማኅበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸውን፣ ማስተባበርና የሚሰጣቸውን ተልእኮ መፈጸም የሚችሉ አካላትን መርጦ ማሰልጠንና ተልእኮ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ይህንንም ለማድረግ በየ አህጉረ ስብከቱ የሚኖሩ ማኅበረሰብ አባላት በጎሳ የሚመሩ መሆኑ፣ ጎሳ መሪዎች ማኅበረሰቡን በመምራትና በማስተባበር ያላቸው ተሰሚነት ማኅበረሰቡን በቤተክርስቲያን አገልግሎት ለመያዝ ያመቻል፡፡ በአካባቢውም ብዙ ጊዜ በአካባቢዎቹ ግጭት ስለሚፈጠር ግጭቱ እንዳይከሰት ከማድረግም አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ የጎሳ መሪዎችን ማሰልጠንና ማሰማራት ከታቻለ ብዙ ወገኖችን መያዝ ይቻላል፡፡ያላመኑትን አስተምሮ አሳምኖ  ማስጠመቅ፣ የተጠመቁትን አዳዲስ አማንያን ደግሞ በምግባር በሃይማኖት በማጽናት ውጤታማ የሐዋርያዊ አገልግሎት መፈጸም ይቻላል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

ለሐዋርያዊ አገልግሎት መስፋፋት በማስተባበርና አገልግሎቱን በመምራት፣ ምእመናንን ማስተባበር የሚችሉ፣ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ አዎንታዊ ተጽእኖ መፍጠር የሚችሉና ቀዳሚ ሚና የሚጫወቱ 300 የጎሳ መሪዎችን/የሀገር ሽማግሌዎችን ማሰልጠንና ተልእኮ መስጠት ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዝርዝር ተግባራት

 • በአህጉረ በጎሳ መሪዎች/የሀገር ሽማግሌዎች የሚተዳደሩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን መለየት
 • የጎሳ መሪዎችን መምረጥ
 • ለጎሳ መሪዎች ጥሪ ማቅረብ
 • አሰልጣኞችን ማዘጋጀት
 • የሥልጠና ማኑዋል ማዘጋጀት
 • የሥልጠና ቦታ ማዘጋጀት
 • የሥልጠና ቁሳቁስ ማሟላት
 • ሥልጠናውን ማከናወን
 • የሥልጠና ሪፖርት ማዘጋጀት
 • ሰልጣኖችን በአገልግሎት ማሰማራት፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

የጎሳ መሪዎች/ሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ በሐዋርያዊ አገልግሎት

የሀገር ሽማግሌዎች/የጎሳ መሪዎች በቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸው ድርሻ ጉልህ ነው፡፡የቤተክርስቲያንን አገልግሎትን በማስተባበር፣ ምእመናንን በመንቀሳቀስ ፣በማስተማር፣ የአጽራረ ቤተክርስቲያንን እንቅስቃሴ በመከታተል እና ሌሎችንም በማገልገል ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የድርሻቸውን መወጣት የሚችሉና አዎንታዊ ተጽእኖ የሚፈጥሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ከሚያጋጥሙት ችግሮች መካከል በተለያዩ ማኅበረሰብ አባላት አለመግባባቶችና ግጭቶች ይፈጠራሉ፡፡እነዚህ የጎሳ መሪዎች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚኖራቸውን ድርሻ ማሰልጠንና ማሰማራት ቢቻል ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መቅረፍ ይቻላል፤ ይህም ለሐዋርየዊ አገልግሎቱ መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

የሀገር ሽማግሌዎች/የጎሳ መሪዎች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ድርሻ ከፍተኛ  ሲሆን በዋናነት የሚከተለውን ያጠቃልላል፡፡

 • ቤተ ክርስቲያንን በአርአያነት የማገልገልና የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
 • የያዙትን ሃይማኖት አጽንተው መያዝ
 • የቤተክርስቲያንን ትምህርት ዘወትር መማርና በምግባረ ክርስትና መጽናት
 • የተማሩትን የቤተክርስቲያን ትምህርት ላልተማሩት ወገኖች ማስተማር
 • ወደ ኦርቶድክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያልመጡ የቤተሰብ አባላት ከአሉ የቤተክርስቲያንን ትምህርት እንዲማሩ ማድረግ
 • በአካባቢው ያሉ የማኅበረሰቡ አባላት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በተከታታይ እንዲማሩ ማስተባበርና ቅስቀሳ ማድረግ
 • የቤተክርስቲያን ትምህርት የተማሩ የማኅበረሰቡ አባላት እንዲጠመቁ ቅስቀሳ ማድረግና ማስተባበር
 • የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲማሩ የሚሰባሰቡበት ቦታ ማዘጋጀት፣ አዳራሽ ለመስራት ማስተባበር
 • የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት ልጆቻቸውን ወደ ቤተክርስቲያን ተምህርት እንዲልኩ ማስተባበርና ቅስቀሳ ማድረግ
 • በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍንና በምእመናን ዘንድ መከፋፈል እንዳይኖር ማድረግ

የሚሰጡ ሥልጠናዎች ዝርዝር

 1. የመዳን ትምህርት 8 ሰዓት
  • ነገረ ድኅነት ምንድ ነው?
  • ከምንድ ነው የምንድነው?
  • እንዴት ዳን?
  • ዘለዓለማዊ ሕይወት
  • የክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አስፈላጊነት
  • ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንና ተሳታፊነት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነት
 2. ነገረ ሃይማኖት /ትምህርተ ሃይማኖት
 3. ሥነ ፍጥረት
 4. የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምንነትና ታሪካ በአጭሩ
 • ኦርቶዶክስ
 • ቤተ ክርስቲያን ትርጉም፣ ባሕርይ ፣ ተልእኮ ፣ታሪክ
 1. የጎሳ መሪዎች ሚና በቤተክርስቲያን አገልግሎት
 2. የግጭት አፈታት

የሥልጠናው በጀት

የዚህ ፕሮጀክት ጠቅላላ 900,000.00 (ዘጠኝ መቶ ሺህ) ብር ሲሆን የበጀት ምንጩም በጎ አድራጊ ምእመናን፣ ማኅበራትና ሰንበት ት/ቤቶች ይሆናሉ።

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50