የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መዝገበ አእምሮ (Ethiopian Orthodox Tewahido Church Encyclopedia) ዝግጅት ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ መጠሪያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መዝገበ አእምሮ (Ethiopian Orthodox Tewahido Church Encyclopedia) ዝግጅት ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ ግብ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትክክለኛ ታሪክና ትውፊት ሰንዶ ማስቀመጥ።

የፕሮጀክቱ ዓላማ

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ጥናትና ምርምር ለማድረግ ለሚፈልግ አካል አጋዥ ማጣቀሻ ማዘጋጀት
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ትክክለኛውን ነገረ እውቀት ለትውልድ ማስተላለፍ
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት ማገዝ

የፕሮጀክቱ ይዘት

የመዝገበ አእምሮው 12 (አሥራ ሁለት) ጥራዞችን (Volumes) ይኖሩታል። አምስት ሺ አበይት ቃላት (Entries) በመጨረሻው ረቂቅ ውስጥ ተካተዋል፡፡

የመጀመሪያውን ጥራዝ ለማሳተም ከሀ – መ በአማርኛ ፊደል ቅደም ተከተል 450 ዓበይት ቃላትን በመለየት ለጸሓፊዎች ተበትነዋል፡፡ ይህ የመጀመሪያው ጥራዝ 1200 ገጾች የሚኖሩት ሲሆን  ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ በቶሎ ተደራሽ እንዲሆን እየተሰራ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ወጪ

የመጀመሪያውን ጥራዝ ለማሳተም የጸሓፍያን፣ የአርታዒያን፣ እና አስተዳደራዊ እና የሕትመት ወጪዎችን ጨምሮ ሶስት ሚሊዮን ብር (3,000,000) በጀት ይጠይቃል፡፡ የተቀሩት አስራ አንድ ጥራዞች እያንዳንዳቸው ከሶስት ሚሊዮን እስከ አምስት ሚሊዮን ብር በጀት ይፈልጋሉ።

አስራ ሁለቱ ጥራዞች በአጠቃላይ ከሰላሳ ስድስት ሚሊየን እስከ አምሳ ስምንት ሚሊየን በጀት ይጠይቃል።

የፕሮጀክቱ የትግበራ ቆይታ ጊዜ

አስራ ሁለቱ ጥራዞች 15 ዓመታት ውስጥ በ2027 ዓ.ም ይጠናቀቃሉ