የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ጥሪ በእሳት ለወደመው ለደብረ ጽዮን ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ገዳም ቤተ ያሬድ የቅኔ ጉባኤ ቤት

የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ጥሪ በእሳት ለወደመው ለደብረ ጽዮን ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ገዳም ቤተ ያሬድ የቅኔ ጉባኤ ቤት

$7,531 of $50,000 raised

በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ደብረ ጽዮን ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ገዳም የሚገኘው የቤተ ያሬድ የቅኔ ጉባኤ ቤት ባጋጠመው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ታላቅ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በጉባኤ ቤቱ የቅኔ፣ የአቋቋም፣ የዜማ፣ የመጽሐፍት እና የቅዳሴ ትምህርት የሚሰጥበት ታላቅ የጉባኤ ቤት ሲሆን በቅኔ ትምህርት ብቻ ከ1,800 በላይ ተማሪዎች በትምህርት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ከ3000 ያላነሱ ደቀ መዛሙርት የሚማሩበት ቤተ ጉባኤ ነው፡፡

በጉዳቱም የመማሪያ አዳራሾችን ጨምሮ ከ200 በላይ የሚሆኑ የደቀመዛሙርቱ መኖሪያ ወድመዋል። ተማሪዎች ለብዙ ጊዜ የደከሙባቸው በእጃቸው የጻፉዋቸው የመመረቂያ ጽሁፎች ተቃጥለዋል፣ በሱባኤው ወቅት ወደ ልምና እንዳይሄዱ ያጠራቀሙት ቀለባቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል፣ ልብሳቸው እና መጽሐፍቶቻቸውም የአደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ በአሁን ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ በችግር ላይ የሚገኙ ሲሆን አስቸኳይ ጊዜያዊ መጠለያ፣ ምግብ እና አልባሳት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ደቀ መዛሙርቱን ከመበተን እንድንታደግ የበረከት ጥሪ ቀርቧል፡፡

 

             

 

 

 

 

 

 

ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

ለቦኬ ጉዶ እና አካባቢ የቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ የገቢ ማሰባሰያ

ለቦኬ ጉዶ እና አካባቢ የቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ የገቢ ማሰባሰያ

$2,730 of $4,000 raised

በማኅበረ ቅዱሳን የዲሲ ንዑስ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ክፍል እና ቀሲስ ምዕራፍ ፀጋዬ ከሚያስተምቸው የመንፈስ ልጆቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ በገጠርና ጠረፋማ ባቢ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ።

“በወንጌልም ማኅበርተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ቆሮ 9፡23

መግቢያ

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ሥር ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ የአቢያተክርስቲያናት ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆን እና የአጥቢያዎች አገልግሎት አሰጣጥ መዳከም፣የስብከተ ወንጌል ዘገምተኛነት የምእመናን ቁጥር መቀነስ እና ወደ እምነቱ መጥተው ጸንተው አለመቆየት፤ ይህን ክፍተት በመጠቀም የሌሎች እምነት ድርጅቶች መስፋፋት በመሰረታዊ ጥናቱ ላይ ተረጋግጧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአብዛኛው የገጠር አካባቢ ቤተክርሰቲያን ተደራሽ ባለመሆኗ እና ሌሎች የእምነት ድርጅቶች ለነዚህ የማሕበረሰብ ክፍሎች አዳራሽ በመስራት ስለሚሰበሰቧቸው እንዲሁም በአካባቢው ያለው የእምነት ተጽዕኖ ሲያደርሱባቸውና አምልኮታቸውን የሚፈጽሙበት አብያተ ክርስቲያናት አለመኖራቸው ከክርስትና እየኮበለሉ ይገኛሉ፡፡

ቦኬ ጉዶ እና አካባቢው ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

የቦኬ ጉዶ መናን ልጅ ወለደው በሥርዓተ-ቤተክርስቲያን በሚፈቅደው ቀን ክርስትና ማስነሳት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የሚያገኙት በእግራቸው ከ4-5 ሰዓት የእግር ጉዞ ተጉዘው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከ60-100 የሚሆኑ ምእመናን ወደ እስልምና መሄዳቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፤ በዚህ አመት በሚያዝያ ወር ብቻ 16 ክርስቲያኖች ሰልመዋል፡፡ የቀሩትም ቃለ እግዚአብሔርን እንዲማሩ በማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ ማእከል በስብከተ ኬላ ፕሮጀክት ታቅፈው ትምህርተ ወንጌልን እያገኙ ይገኛሉ፡፡ በስብከተ ኬላ ትምህርተ ወንጌልን እንኳን ቢያገኙ ልጆቻቸውን ክርስትና የሚያስነሱበት፣ ለሞተ፦ የስጋው ማረፊያ የሚሆን የመቃብር ቦታ፣ ስጋወ ወደሙ የሚቀበሉበት ቤተክርስቲያን የላቸውም፡፡

ቦኬ ጉዶ እና አካባቢው ወደፊት መተግበር ያለባቸው ዓበይት ተግባራት

የቦኬ ጉዶ የስብከተ ኬላ 57 አባወራ ያሉበት እና ለቤተክርስቲያን መስርያ ቦታ ባያገኙም መሬት ለመግዛት የባንክ አካዉንት ከፍተዉ ገንዘብ በማሰባሰብ መሬት መገዛት ችለዋል፡፡ከአሁን በፊት ትንሽ ስፍራ የነበራቸዉ ቢሆንም ስፍረዉን በሙስሊሞች በመነጠቅ መሰብሰቢያ ቦታ የሌላቸዉ በመሆኑ እርሻ ዉስጥ ዛፍ ስር እየተሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ገንዘብ በመሰብሰብ የቤተክርስቲያን ቦታ ተገዝቶ ለህንጻ ቤተክርስቲያን ለመሥራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የቦኬ ጉዶ ምእመናን ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ የሚኖሩ አርሶአደሮች በመሆናቸው በራሳቸው ቤተክርስቲያን መስራት የማይችሉ ናቸው፡፡ መስሪያ ገንዘብ ስላልተገኘ ባዶ መሬት ይገኛል፡፡ስለሆነም ይህንን ክፍተት ለመሙላት ይህ ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህ በእግዚያብሔር አምሳል የተፈጠሩ ወገኖቻችን በሰው ልጆች ዘንድ የሚናፈቀውን የእግዚያብሔርን ቃል መስማት እና ለቅድስናው ተቋዳሽ እንዲሆኑ ለማድረግ በአቅራቢያቸው ቤተክርስቲናትን ማነፅ ተገቢና ቤተክርስቲያናችን ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ ነው፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

ድረሱልንና አብረን መንግስቱን እንውረስ

ድረሱልንና አብረን መንግስቱን እንውረስ

Thank you to all our donors, we have met our fundraising goal.

4ኛው ዙር የሐዊረ ሕይወት በቤትዎ በአሜሪካ

4ኛው ዙር የሐዊረ ሕይወት በቤትዎ በአሜሪካ

$15,415 of $100,000 raised
$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $20

ሐዊረ ሕይወት

ሐዊረ ሕይወት ወይም የሕይወት ጉዞ ፥ መንፈሳዊ ሕይወት ለማጠንከር ምእመናንን በማሳተፍ ወደ ቅዱሳት መካናት የሚደረግ ጉዞ እና መርሐ ግብር ነው። በመርሐ ግብሩ ትምህርተ ወንጌል ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት ዙሪያ ውይይት፣ ለጥያቄዎ መልስ፣ እና መዝሙር የተካተቱ ሲሆን ከዕለት ዕለት ሥራና ከዓለም ውጣ ውረድ ራቅ ብለው ፤ ከሚጎበኙት አዲስ ቦታ ህሊናን እያዝናኑ ፤ ከቦታው በረከት እየተቀበሉ ታድሰው የሚመለሱበት ነው።

ነገር ግን በዚህ ዓመት በኮቪድ  19 ወረርሽኝ ምክንያት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የ ሐዊረ ሕይወት መርሃግብር በቤታችን ወይም ባለንበት ሆነን መሳትፍ በምንችልበት ሁኔታ ተዘጋጅቶ ቀኑን በጉጉት እየጠበቅን እንገኛልን።

4ኛው ዙር የሐዊረ ሕይወት (የሕይወት ጉዞ)

የዚህ ዓመት የሐዊረ ሕይወት ሐዊረ ሕይወት በቤትዎ በአሜሪካ” የሚል ስያሜ ተስጥቶታል።

የዕለቱ መርሐ ግብር የሚከተሉትን እና ሌሎችንም ያካትታል።

  • ቃለ ምዕዳን እና መልዕክታት በብጹዓን ሊቀ ጳጳሳት
  • ትምህርተ ወንጌል በተጋባዥ መምራን
  • ለጥያቄዎችዎ መልስ የሚያገኙበት በምክረ አበው ዝግጅት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መልስ ይሰጥባቸዋል
  • ዝማሬ በተጋባዥ ዘማሪያን
  • በማህበሩ እየተከናወኑ ያሉ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎቶች

ቀን ፡ ጥቅምት 7, 2013 (October 17, 2020)
ሰዓት፡ 3 pm – 8pm EST | 2 pm -7 pm CST|12 pm -5 pm PST

ለህጻናት እና አዳጊዎች፡ 11 am -2pm | 10 am -1 pm CST| 8 am -11AM PST  በአማርኛ እና በ እንግሊዝኛ የተለያዩ ዝግጅቶ

በመርሐግብሩ ላይ ጥያቄ ካላችሁ በስልክ ቁጥር፡ 1(703) 307 6686 ልትደውሉልን እንዲሁም በኢሜል፡  dc@eotcmk.org or virginia@eotcmk.org ልትጽፉልን ትችላላችሁ።

4ኛው ዙር የሐዊረ ህይወት የቲኬት ዋጋ

ከ $10 ጀምሮ ለበረከት እየከፈሉ ይሳተፉ። የሚገኘው ገቢ ኢትዮጵያ እየተከናወኑ ለሚገኙ የሐዋሪያዊ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ይውላል።

 

           

የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስብከተ ወንጌል አገልግሎት ይደግፉ

የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስብከተ ወንጌል አገልግሎት ይደግፉ

$700 of $25,000 raised

በወንጌልም ማኅበርተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ቆሮ 923

 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊት ናት፡፡ አስተምህሮዋና መሠረተ እምነቷ ከአማናዊው መምህር ከኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘ በመሆኑ አማናዊትና ርትዕት ናት፡፡ የዚህች ርትዕት ቤተ-ክርስቲያን ዋነኛ አገልግሎቷም ሐዋርያዊ ተልእኮ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታ በአካል የተማሩትን የምስራች ቃል በታዘዙትና በተሰጣቸዉ መንፈሳዊ ኃይል በመታገዝ በብዙ መከራ ዉስጥ ሆነዉ በዓለሙ ሁሉ ዞረዉ አስተምረዋል፤ነፍሳትንም ለክርስቶስ ማርከዋል፡፡

ይሁን እንጂ ቤተ-ክርስቲያናችን “ወርቃማ” ተብለው የሚጠሩ ዘመናትን ያሳለፈች ቢሆንም፣ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጊዜያትንም አሳልፋለች፡፡በዚህም የተነሳ የስብከተ ወንጌል/የሐዋርያዊ አገልግሎት ተደራሽነት እጅግ ውሱን እና የተቋረጠ እንድሆን አድርጎታል፡፡ይህ የአገልግሎት ውሱንነት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሚናፍቁ በገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች መድረስ እንዳይቻል አድርጎታል፡፡ ይህም መናፍቃኑ ቀድመው በመግባት ብዙዎችን ወደ ምንፍቅና እንዲወስዷቸው በር ከፍቶላቸዋል፡፡ብዙ ወገኖች እውነተኛውን የወንጌል ብርሃን ሳይመለከቱ በእግዚአብሔር ቃል ሳይጸኑ ፣ በገጠር በጠረፋማው የሀገራችንና በአጠቃላይ የዓለማችን ክፍል ተበትነው ፣ ድኅነትን እንደናፈቁ ፣ በጎውን ነገር ሳያዩ ሞተ ሥጋ ይቀድማቸዋል፡፡

በገጠርና ጠረፋማ አከባቢ የሚገኙ ወገኖችን መልካሙን መንገድ የሚያሳያቸው አጥተው ወደ ሌሎቸ የእምነት ቤቶች የሚሄዱትን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለማምጣት፣ አስተምሮ ለማስጠመቅ እና የሥላሴን ልጅነት ያገኙትን ምዕመናን የቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት አግኝተው በምግባር በሃይማኖት እንዲጸኑ ለማድረግ ከአዳዲስ አማንያኑ መካከል የቅድስት ቤተክርስቲያን አገልጋይ ማፍራት ይጠበቃል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስብከተ ወንጌል አገልግሎት በመደገፍ የወንጌል ማኅበርተኛ ይሁኑ!!!”

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እና መጠነኛ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ

Thank you for visiting. We are no longer accepting donations.