የቅዱሳት መካናት ፕሮጀክቶች

የበደሌ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት

የበደሌ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት

$500 of $115,385 raised

ይህ ፕሮጀክት ማኅበረ ቅሳን በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ለሚተገብራቸው ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች እንዲውል 545 ካ.ሜ ስፋት ያለው ቦታ ከወ/ሮ ካሰች ገ/እግዚአብሔር የተበረከተ ሲሆን ማኅበሩ ለ2 ተከታታይ ዓመታት ከ50 በላይ ተተኪ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሥልጠናዎችን እንዲያገኙና የትምህርተ ሃይማኖት ኮርሶችን እንዲማሩ በማድረግ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ፤ ምእመናን በሃይማታቸው እንዲጸኑ ማድረግ ተችሏል፡፡

ነግር ግን በቦታው ላይ የሚገኙ ቤቶች የአረጁ በመሆናቸው ዘመኑን በሚፈቅደው መልኩ ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት በመተግበር ቦታውን ለታለመለት ዓላማ ማዋል ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረትም ማኅበረ ቅዱሳን በጥናት ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለፕሮጀክቱ የሚየስፈልገው ገንዘብ ወደፊት የሚታወቅ ይሆናል፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

በወቅታዊ ጉዳዮች ጉዳት ለደረሰባቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች አስቸኳይ ድጋፍ

በወቅታዊ ጉዳዮች ጉዳት ለደረሰባቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች አስቸኳይ ድጋፍ

$200 of $102,194 raised

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤቶች ደቀ መዛሙርትን በትምህርትና በምግባር አንፀው የነገውን ካህን፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና መሪ የሚያፈሩ ተቋማት ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷ ከ100 ሺህ በላይ የአብነት ተማሪዎች ያሏት ሲሆን የቤተክርስቲያኗን እምነትና ሥርዓት ለመጠበቅ የአብነት ትምህርት ቤቶች ዐቢይ ሚና አላቸው፡፡

 

ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦች ምክንያት እነዚህ ትምህርት ቤቶች ትኩረት ስለተነፈጋቸው ሕልውናቸው አደጋ ተጋርጦበት ቆይቷል፡፡ ስለ ምእመናን ድኅነት፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን እምነትና አስተምህሮ መጠበቅ ያለ በቂ መተዳደሪያ የድርሻቸውን እየተወጡ የሚገኙትን የአብነት መምህራን፤ ከቀያቸው ተሰደው፣ ከወላጆቻቸው ርቀው፣ በእንተ ስማ ለማርያም ብለው ቁራሽ ለምነው ጎጆ ቀልሰው አልያም በመቃብር ቤት ሆነው ሕይወትን ለመስጠት ሕይወት የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር በችግር በመማር ላይ  ይገኛሉ፡፡

በተለይም አሁን ባለዉ ሀገራዊ ወቅታዊ ጦርነት ምክንያት ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ችግሩ ከመከሰቱ በፊት በአካባቢዉ ማህበረሰብ ድጋፍ ሲማሩ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ህብረተሰቡም እነሱን ሊረዳ ቀርቶ ራሱም ችግር ላይ በመዉደቁ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶችን ችግሩ እስኪረጋጋ ድረስ ጊዜያዊ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ።

ዋና ዓላማ

ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች በወቅታዊ ችግር ምክንያት ገዳማቸዉ እንዳይፈታ እና ጉባኤያቸዉን እንዳያጥፉ በማድረግ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲቀጥል ማድረግ እና አገልጋዮችን እንዲያፈሩ ማስቻል፤

ዝርዝር ዓላማ፡

 • በቀለብ ችግር ምክንያት አብነት ተማሪዎች ተስፋ ቆርጠዉ ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ለማድረግ፤
 • መነኮሳት ገዳማቸዉን ጥለዉ እንዳይሰደዱ ማድረግ
 • በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት የወደሙባቸዉን ንብረቶች በጊዜያዊነት እንዲተኩ ለማስቻል፤

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

አርአያ ገዳማት ፕሮጀክት

አርአያ ገዳማት ፕሮጀክት

$0 of $922,115 raised

ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማት የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችን በመተግበር መነኮሳት በበአታቻው ጸንተው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለትውልድ እንዲያስተላለፍ፡ ለማድረግ የበኩልን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል፡፡ እነዚህ ገዳማት ከኢኮኖሚያዊ ዕድገት በተጨማሪ በሁለንታዊ መልኩ ጠንካራ አርአያ በማድረግ የኅዙናን መጠጊያ፣ የደካሞች ማረፊያ፣ የሰላም አምባ፣ የትምህርት ማእከል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረትም ማኅበረ ቅዱሳን አርአያ ገዳማት ፕሮጀክት ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ፡የአርአያ ገዳማት ፕሮጀክት 3 ዋና ዋና ዓለማዎች አሉት

 1. የተመረጡ ገዳማትን ጠንካራ ገዳማዊ ሥርዓት እንዲኖራቸው ማድረግ፣
 2. ገዳማዊ ሥርዓት ያላቸው በኢኮኖሚ አቅማቸው ጠንካራ ማድረግ
 3. ለአካባቢው ማኅበረሰብ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ

በዚህ መሠረትም የአርአያ ገዳማት ፓኬጅ ትግበራ በ8 ገዳማት የሚጀመር ዚሆን ጥሩ ተመክሮ ያላቸው ገዳማት ሌሎች እንዲያካፍሉና በገዳማት መካከል እርስ በእርስ ግንኙነት ለመፍጠር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርት እድል ፕሮጀክት

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርት እድል ፕሮጀክት

$0 of $75,539 raised

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ማእከል ሆና ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚያስፈልጋትን የሰው ሀይል በእውቀት መግባ በስነ ምግባር ኮትኩታና አሳድጋ አበርክታለች፡፡ በዚህም ለቤተ ክህነት እና ቤተ መንግሥት ከአገልጋይ ካህናት እስከ ቅዱሳን ነገሥታት ማፍራት ችላለች፡፡ ነገር ግን ይህ አስተዋጽኦ በተለያዩ ጊዜ በተነሱ ስሁት ርዕዮተ ዓለማዊ ፈተናዎች እየተዳከመ የመጣ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ችግሩን ተረድቶ የአብነት ትምህርትና ዘመናዊ (አስኳላ) ትምህርት ተናበው እንዲሔዱ ሁለቱም ለቤተክርስቲያንና ለሀገር የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ በሁለት በኩል የተሳሉ አገልጋዮች እንዲፈሩ ለማድረግ በታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ (ዳግማዊ ቄርሎስ) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተሰየመ ነጻ የትምህርት እድል (scholarship) መርሐ ግብር ቀርጾ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በማድረግ ልዩ ልዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ እና ተጨባጭ ለውጦች ማምጣት ተችሏል፡፡ በዚህ መሠረትም ከዘመናዊ ወደ አብነት ትምህርት ቤት የሚገቡ የነጻ የትምህርት እድሉ ተጠቃሚዎች በተመረጡ ጉባኤ ቤቶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚደረግ ሲሆን ከአብነት ወደ ዘመናዊ እንዲሁም በመንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲማሩ እድሉ የተሰጣቸው መምህራንና ደቀመዛሙርት በተመደቡበት የትምህርት ተቋም ወጪያቸውን በመሸፍን እንዲማሩ ይደረጋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

 • በትውልዱ መካከል የተከፈተውን ክፍተት (ከ1960 ዎቹ በኋላ ከቤተመንግስትና ቤተ ክህነት መለያየት በኋላ) ይሞላል ድልድይ ሆኖ ያገናኛል፤
 • ለቤተ ክርስቲያን ተተኪ መሪዎችን ከማፍራት አንጻር አስተዋጽኦው የጎላ ነው፡፡
 • ዓለም አቀፍ አገልግሎት እና ሐዋርያዊ ተልእኮ ከመፈጸም አንጻር የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
 • የአብነት ትምህርትን በትውልዱ ከማስፋፋትና ተወዳጅ ከማድረግ አንጻር ጠቀሜታው ሰፊ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

ሁለንተናዊ አቅምና ዝግጁነት ያላቸው በስነ ምግባር የታነጹ አገልጋዮችንና መሪዎችን ለቤተክርስቲያን ብሎም ለሀገራችን ማፍራት፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የመነኮሳት፣ የአብነት መምህራን እና ተማሪዎች ሁለንተናዊ አቅም ማሳደጊያ ሥልጠና ፕሮጀክት

የመነኮሳት፣ የአብነት መምህራን እና ተማሪዎች ሁለንተናዊ አቅም ማሳደጊያ ሥልጠና ፕሮጀክት

$0 of $31,904 raised

በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የሚገኙ መነኮሳት የአብነት መምህራንና ተማሪዎች ትውልዱን በሃይማኖት ከማጽናት፣በእውቀትና በስነ ምግባር ከመቅረጽና ከማነጽ አንጻር ሚናቸው የጎላ ሲሆን ዘመኑን የዋጁ፣ሁለንተናዊ ዝግጁነት እና አንጻራዊ ምሉእነት እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሥልጠናው በደረጃ ተከፋፍሎ ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ሦስት ለመነኮሳት የአብነት መምህራንና ደቀመዛሙርት የሚሰጥ ሲሆን ለእያንዳንዱ ደረጃ የሚመጥን መምህራንንና ደቀመዛሙርትን ታሳቢ ያደረገ የሥልጠና ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡ በተጨማሪ ተሞክሮዎችና ተግባራዊ የልምድ ልውውጦች ይደረጋሉ፡፡ ስለሆነም የመምህራን እና ደቀመዛሙርትን ሁለንተናዊ አቅምና ዝግጁነት በማሳደግ ለስብከተወንጌልና ለሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ላይ የመሪነት ሚና እንዲኖራቸው ዝግጁ ለማድረግ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ፕሮጀክት አስፈልጓል፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

መነኮሳትን የአብነት መምህራን እና ደቀመዛሙርትን አቅም በማሳደግ በቀጣይ ለሚኖረው ሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን አገልግሎትና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዝግጁ ማድረግ፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ሁለገብ የሕንጻ ፕሮጀክት

የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ሁለገብ የሕንጻ ፕሮጀክት

$0 of $450,388 raised

የቅዱስ ያሬድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዐተ አምልኮዋ የምትጠቀምባቸው መጻሕፍትን ዜማ በመድረስ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመድረስ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉልህ ድርሻ ከአበረከቱት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መካከል አንድ ነው፡፡ የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በሰሜን ጎንደር በራስ ደጀን አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ገዳሙ ረጅም እድሜና  ታሪክ ያለው የተከበረ ቦታ ነው፡፡ ይህንን ታሪክ ጠብቆ ለማቆየት ደግሞ የገዳሙ መሠረታዊ ችግሮች ሊፈቱ ይገባል፡፡ የፕሮጀክቱ ጥናት በተከናወነበት ወቅት በገዳሙ ስልሳ  (43 መነኮሳት እና 17 መነኮሳይያት)፣ 13 ዲያቆናት እና 5 ቀሳውስት ይገኛሉ፡፡ በገዳሙ ውስጥ 30 ተማሪዎች የአብነት ትምህርት ሲማሩ የነበሩ ቢሆንም በአካባቢው ባለው ችግር ምክንያት ገዳሙን ለቀው ወጥተዋል፡፡ በዚህ መሠረትም ማኅበረ ቅዱሳን ገዳሙን ለማጠናከር ከደባርቅ ከተማ አስተዳደር 1000 ካ.ሜ ለንግድ የሚሆን ቦታ የተረከበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሕንጻው የሚያርፈው 500 ካሬ ሜትር ላይ  ነው ፡፡  ቀሪው ለግቢ እና ለመሳሰሉት ሥራ የሚውል ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

 • የገዳሙን መንፈሳዊ አገልግሎት በማጠናከር ማኅበረ መነኮሳቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ለገዳሙ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በልመና ከማሟላት ይልቅ መንፈሳዊ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማድረግ፣
 • የአብነት ተማሪዎቹን እና መምህራኑን የምግብ እና የአልባሳት ችግሮችን በመፍታት ለቤተ ክርስቲያን ተተኪ ማፍራት፣
 • የገዳማውያንን ፍልሰት በማስቀረት ገዳሙ እንዳይፈታና ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር ማድረግ የሚሉት ናቸው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

ገዳሙ በገቢ እራሱን እንዲችል ማድረግ፣ መንፈሳዊ አገልግሎቱ ጠንካራ እንዲሆን እና ማኅበረ መነኮሳት (መነኮሳት እና መነኮሳይያት) በበዓታቸው ጸንተው እንዲኖሩ እና የቤተ ክርስቲያን ተተኪ የአብነት ተማሪዎችን ማፍራት ነው፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤት ማቋቋሚያ ፕሮጀክት

ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤት ማቋቋሚያ ፕሮጀክት

$150 of $120,908 raised

በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ይህ የፕሮጀክት ጥናት መረጃ እስከተወሰደበት ጊዜ ድረስ በ18 ወረዳ ቤተክህነቶች የተዋቀረና በአጠቃላይ 382 የሚደርሱ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ ከአሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል 55 (14 በመቶ) ምንም አገልጋይ የሌላቸውና አገልግሎትም የማይሰጥባቸው ሲሆን፤ አገልጋይ ያልተሟላላቸውና በከፊል አገልግሎት የሚሰጥባቸው ደግሞ 300 (78.5 በመቶ) ናቸው፡፡ የተሟላ ቀሳዉስትና ዲያቆናት ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት 27 ናቸዉ፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት፡

 • የቤተክርስቲያን ተረካቢ የሚሆኑ የአካባቢውን ልጆች በማስተማር ቀሳውስት እና ዲያቆናትን በሚፈለገው መጠን ለማፍራት፤
 • የአብነት ትምህርት ቤቱ በየሁለት ዓመቱ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር በሀገረ ስብከቱ በአገልጋይ እጦት ምክንያት የተጓደለውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጠናከር እና የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ ማድረግ
 • ለምዕመናኑ በቂ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት፤ በቋንቋቸው ወንጌል በማስተማር ያመኑትን በሃይማኖታቸው ፀንተው እንዲቆዩ ለማድረግና የጠፉትን ለመመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ፡

በሀገረ ስብከቱ አዲስ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ በማካሄድ ቀሳውስት እና ዲያቆናት በማፍራት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ እና የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ይዘት፡

የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የአብነት ት/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት በውስጡ የሚይዘው

 • ለ40 ተማሪዎች ማደሪያ የሚያገለግል ባለ አምስት ክፍል አንድ ቤት
 • 40 ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል አንድ ጉባዔ ቤት
 • ለ40 ተማሪዎች የሚያገለግል ባለ ስድሰት ክፍል አንድ መፀዳጃ ቤት

ለአብነት ት/ቤቱ የምግብ ማብስያና ዕቃ ማስቀመጫ የሚያገለግል ባለሁለት ክፍል አንድ ቤት።

 

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50

የጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምህረት የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት

የጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምህረት የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት

$7,500 of $307,000 raised

 

. የፕሮጀክቱ አጠቃላይ መረጃ

 • የፕሮጀክቱ ስም፡– ጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐብየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ መርቆሪዎስ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት
 • ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት /ስብከት፡ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት
 • ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡– ሐምሌ 25/ 2014 ዓ.ም
 • ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡- ነሐሴ 30/ 2015 ዓ.ም
 • የፕሮጀክቱ አጠቃላይ በጀት፡ 16,000,250.31 (አስራ ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ከ 31 ሳንቲም)
 • የፕሮጀክቱ አፈጻጸም፡ 10%
 • የፕሮጀክቱ ድጋፍ አድራጊ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ በጎ አድራጊ ምእመናን ድጋፍ አድራጊነት የሚተገበር ፕሮጀክት ነው፡

. የፕሮጀክቱ አጭር መግለጫ

ከጎንደር ከተማ ታሪክ ጋር የተያያዘዉ የደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምህረት ወቅዱስ መርቆሪዎስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በፈጻሜ መንግሥት በአጼ ተክለጊዮርጊስ (ከ1772 እስከ 1777 ዓ.ም) ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ሲሆን ተካዩ በወቅቱ የኢትዮጲያ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት የሰሜኑ ገዥ ራስ ቢትወደድ ገብሬ ናቸዉ፡፡ ከአቃቤ ሰዓት ከብቴ አራቱን ጉባኤያት የተማሩት ሊቅ መምህር ወልደ አብ የደብሯን አለቃነት ደርበው በማስተዳደር የመጽሕፍተ ብሉያት ጉባኤ ቤት በ1773 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡ መምህር ወልደ አብም ለደብሩ የመደቡትን የብሉያትን ጉባኤ መደበኛ አድርገው ሌሎችንም ሦስቱን ማለትም ሐዲሳትን ሊቃውንትን እና መነኮሳትን በመጨመር በርካታ ሊቃውንትን አፍርተዋል፡፡ ከመምህር ወልደ አብ ጀምሮ እስካሁን ድረስ 16 መምህራን በጉባኤ ቤቱ ወንበር ዘርግተው የአስተማሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት መምህር ፍሬሕይወት አራጌ ከ60 በላይ ደቀመዛሙርትን እያስተማሩ ይገኛሉ።

ጉባኤ ቤቱ ከዚህ በላይ ተቀብሎ መስተማር የሚጠበቅበት ቢሆንም የተማሪዎች እና የመምህራን መኖሪያ ቤት፤ የጉባኤ (መማሪያ) ቤት፤ የቤተ መጻሕፍትና የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ቦታ ችግር ስላለበት በሚፈለገው መጠን ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ አልቻለም፡፡ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን የጉባኤ ቤቱን ችግሮች ለመፍታት ይህን ፕሮጀክት ቀርጾ መተግበር አስፈላጊ ሆኗል።

. የፕሮጀክቱ ግብ

ዘመኑን የዋጀ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን በማፍራት የቤተክርስቲያን አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ፡፡

. የፕሮጀክቱ ዓላማ

 • በአብነት ት/ቤቱ ያለውን የማደሪያ ቤት፣ የጉባኤ ቤት፣ የቤተ መጻሕፍት እና የሥልጠና ቦታ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ባለ 2 ወለል ሕንጻ መገንባት፡
 • ከትምህርቱ ጎን ለጎን ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች በመስጠት በሁለተናዊ መልኩ ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ።

. በፕሮጀክቱ የደረሰበት ደረጃ)

በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ግንባታ 15% የደረሰ ሲሆን የመሠረት ሥራዎች ተጠናቀው የግራውንድ ኮለን በመሠራት ላይ ይገኛል፡፡

 

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50