ለቦኬ ጉዶ እና አካባቢ የቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ የገቢ ማሰባሰያ

ለቦኬ ጉዶ እና አካባቢ የቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ የገቢ ማሰባሰያ

$2,730 of $4,000 raised

በማኅበረ ቅዱሳን የዲሲ ንዑስ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ክፍል እና ቀሲስ ምዕራፍ ፀጋዬ ከሚያስተምቸው የመንፈስ ልጆቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ በገጠርና ጠረፋማ ባቢ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ።

“በወንጌልም ማኅበርተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ቆሮ 9፡23

መግቢያ

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ሥር ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ የአቢያተክርስቲያናት ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆን እና የአጥቢያዎች አገልግሎት አሰጣጥ መዳከም፣የስብከተ ወንጌል ዘገምተኛነት የምእመናን ቁጥር መቀነስ እና ወደ እምነቱ መጥተው ጸንተው አለመቆየት፤ ይህን ክፍተት በመጠቀም የሌሎች እምነት ድርጅቶች መስፋፋት በመሰረታዊ ጥናቱ ላይ ተረጋግጧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአብዛኛው የገጠር አካባቢ ቤተክርሰቲያን ተደራሽ ባለመሆኗ እና ሌሎች የእምነት ድርጅቶች ለነዚህ የማሕበረሰብ ክፍሎች አዳራሽ በመስራት ስለሚሰበሰቧቸው እንዲሁም በአካባቢው ያለው የእምነት ተጽዕኖ ሲያደርሱባቸውና አምልኮታቸውን የሚፈጽሙበት አብያተ ክርስቲያናት አለመኖራቸው ከክርስትና እየኮበለሉ ይገኛሉ፡፡

ቦኬ ጉዶ እና አካባቢው ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

የቦኬ ጉዶ መናን ልጅ ወለደው በሥርዓተ-ቤተክርስቲያን በሚፈቅደው ቀን ክርስትና ማስነሳት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የሚያገኙት በእግራቸው ከ4-5 ሰዓት የእግር ጉዞ ተጉዘው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከ60-100 የሚሆኑ ምእመናን ወደ እስልምና መሄዳቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፤ በዚህ አመት በሚያዝያ ወር ብቻ 16 ክርስቲያኖች ሰልመዋል፡፡ የቀሩትም ቃለ እግዚአብሔርን እንዲማሩ በማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ ማእከል በስብከተ ኬላ ፕሮጀክት ታቅፈው ትምህርተ ወንጌልን እያገኙ ይገኛሉ፡፡ በስብከተ ኬላ ትምህርተ ወንጌልን እንኳን ቢያገኙ ልጆቻቸውን ክርስትና የሚያስነሱበት፣ ለሞተ፦ የስጋው ማረፊያ የሚሆን የመቃብር ቦታ፣ ስጋወ ወደሙ የሚቀበሉበት ቤተክርስቲያን የላቸውም፡፡

ቦኬ ጉዶ እና አካባቢው ወደፊት መተግበር ያለባቸው ዓበይት ተግባራት

የቦኬ ጉዶ የስብከተ ኬላ 57 አባወራ ያሉበት እና ለቤተክርስቲያን መስርያ ቦታ ባያገኙም መሬት ለመግዛት የባንክ አካዉንት ከፍተዉ ገንዘብ በማሰባሰብ መሬት መገዛት ችለዋል፡፡ከአሁን በፊት ትንሽ ስፍራ የነበራቸዉ ቢሆንም ስፍረዉን በሙስሊሞች በመነጠቅ መሰብሰቢያ ቦታ የሌላቸዉ በመሆኑ እርሻ ዉስጥ ዛፍ ስር እየተሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ገንዘብ በመሰብሰብ የቤተክርስቲያን ቦታ ተገዝቶ ለህንጻ ቤተክርስቲያን ለመሥራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የቦኬ ጉዶ ምእመናን ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ የሚኖሩ አርሶአደሮች በመሆናቸው በራሳቸው ቤተክርስቲያን መስራት የማይችሉ ናቸው፡፡ መስሪያ ገንዘብ ስላልተገኘ ባዶ መሬት ይገኛል፡፡ስለሆነም ይህንን ክፍተት ለመሙላት ይህ ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህ በእግዚያብሔር አምሳል የተፈጠሩ ወገኖቻችን በሰው ልጆች ዘንድ የሚናፈቀውን የእግዚያብሔርን ቃል መስማት እና ለቅድስናው ተቋዳሽ እንዲሆኑ ለማድረግ በአቅራቢያቸው ቤተክርስቲናትን ማነፅ ተገቢና ቤተክርስቲያናችን ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ ነው፡፡

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50