የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ጥሪ በእሳት ለወደመው ለደብረ ጽዮን ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ገዳም ቤተ ያሬድ የቅኔ ጉባኤ ቤት

የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ጥሪ በእሳት ለወደመው ለደብረ ጽዮን ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ገዳም ቤተ ያሬድ የቅኔ ጉባኤ ቤት

$7,531 of $50,000 raised

በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ደብረ ጽዮን ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ገዳም የሚገኘው የቤተ ያሬድ የቅኔ ጉባኤ ቤት ባጋጠመው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ታላቅ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በጉባኤ ቤቱ የቅኔ፣ የአቋቋም፣ የዜማ፣ የመጽሐፍት እና የቅዳሴ ትምህርት የሚሰጥበት ታላቅ የጉባኤ ቤት ሲሆን በቅኔ ትምህርት ብቻ ከ1,800 በላይ ተማሪዎች በትምህርት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ከ3000 ያላነሱ ደቀ መዛሙርት የሚማሩበት ቤተ ጉባኤ ነው፡፡

በጉዳቱም የመማሪያ አዳራሾችን ጨምሮ ከ200 በላይ የሚሆኑ የደቀመዛሙርቱ መኖሪያ ወድመዋል። ተማሪዎች ለብዙ ጊዜ የደከሙባቸው በእጃቸው የጻፉዋቸው የመመረቂያ ጽሁፎች ተቃጥለዋል፣ በሱባኤው ወቅት ወደ ልምና እንዳይሄዱ ያጠራቀሙት ቀለባቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል፣ ልብሳቸው እና መጽሐፍቶቻቸውም የአደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ በአሁን ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ በችግር ላይ የሚገኙ ሲሆን አስቸኳይ ጊዜያዊ መጠለያ፣ ምግብ እና አልባሳት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ደቀ መዛሙርቱን ከመበተን እንድንታደግ የበረከት ጥሪ ቀርቧል፡፡

 

             

 

 

 

 

 

 

ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50