ይለግሡ – የዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የሐዲሳትና ፍትሐ ነገሥት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት

ይለግሡ – የዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የሐዲሳትና ፍትሐ ነገሥት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት

$11,815 of $109,110 raised

መግቢያ

 የአብነት ትምህርት ቤቶች የሚባሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮዋንና ሥርዐተ አምልኮዋን የሚፈጽሙ ካህናት (ዲያቆናት፣ቀሳዉስትና ኤጲስ ቆጶሳት) እና ሊቃዉንትን የሚፈሩበት የትምህርት፣ የሥልጠና እና የምርምር ተቋማት ናቸው፡፡ በእነዚህ ተቋማትም የንባብ፣ የዜማ፣ የአቋቋም፣ የቅኔ፣ የትርጓሜ መጻሕፍትና የቁጥር /አቡሻኸር/ ወዘተ ትምህርቶች ይሰጥባቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ የአብነት ትምህርት ወደ አዲስና ታላቅ ምዕራፍ የተሸጋገረዉ 6ተኛው ክ/ዘ በተነሣዉና የመጻሕፍትና የዜማ ደራሲ በሆነው በታላቁ ሊቅ ቅዱሰ ያሬድ አማካኝነት ነዉ፡፡ ከ12ኛው እስከ 15ተኛው ክ/ዘ የነበረዉ ዘመን ሊቃዉንተ ቤተክርስቲያን በብዛት የተነሱበትና መጻሕፍትም የተጻፉበት ዘመን የነበረ ሲሆን ከግራኝ ዘመን በኀዋላ ዳግም የአብነት ትምህርት ቤቶች የተስፋፉት በ17ኛው ክ/ዘመን ነበር፡፡

የአብነት ትምህርት ቤቶች በተለይም ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ሰዎች ማንበብ፣ መጻፍ፣ ስዕል፣ቅርጻ-ቅርጽ፣ምህንድስና፣ ፍልስፍና፣ ታሪክ፣ ሕግ፣አስተዳደር፣ ሕክምናና ሌሎች ጥበባትን የሚማሩት ከአብነት ት/ቤቶች ነበር፡፡ ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች በተገኘው ተዳሳሽና የማይዳስሱ የፈጠራና የኪነጥበብ ዉጤቶች ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም ጭምር አማራጭ የገቢ ምንጭና የመልካም ገጽታ ግንባታ ማዕከላት ሆነዉ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶች የቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርት ሳይበረዝና ሳይከለስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር በማድረግ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ህልውናና ለምእመናን ተገቢውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ ሚና አላቸዉ፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን በ2003/4 ዓ.ም. በተሰበሰበዉ መረጃ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከ2348 በላይ የአብነት ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ ከአነዚህ መካከል አንዱ የዲማ ቅዱስ ጎዮርጊስ ጉባኤ ቤት ነው፡፡ በመሆኑም ተተኪ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ለማፍራት የአብነት ትምህርት ቤቶችን በማጠናከር አስፈላጊ ሆኗል፡፡

 1. የዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብነት /ቤት መረጃ

የዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የተመሰረተዉ በ1297 ዓ.ም በአፄ አምደፅዮን ዘመነ መንግሥት ሲሆን የመሠረቱትም አባ በኪሞስ (አባ ተከስተ ብርሃን) ነው፡፡ ገዳሙ በምስራቅ ጎጃም ገረ ስብከት በቢቸና ወረዳ ከአዲስ አበባ በ265 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ 78 መምህራን በአበምኔትነት አገልግለዉታል፡፡ በገዳሙ 7 ጉባኤ ቤቶች ማለትም የንባብና ቁጥር ትምህርት ቤት ፣የቅዳሴ ትምህርት፣ የድጓ ትምህርት ቤት ፣ የአቋቋም ትምህርት ቤት፣ የሐዲሳትና ፍትሐ ነገስት ትምህርት ቤት፣ የቅኔ ትምህርት ቤት፣ የቅዳሴ ትምህርት ቤት የሚገኙ ሲሆን የቅኔ ጉባኤ ቤት መምህርት ሴት መነኮስ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በ7ቱ ጉባኤ ቤቶች 330 ተማሪዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ 300 ወንዶች ሲሆኑ 30 ደግሞ ሴቶች ናቸዉ፡፡

አብዛኛው ተማሪዎች በእንተ ስማ ለማርያም በማለት ለምነዉ እና የቀን ሥራ በመሥራት የዕለት እንጀራቸውን የሚያገኙ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ለ65 ተማሪዎች እና 4 መምህራን ለምግብ  ወርኃዊ የገንዘብ ድጎማ ያደርጋል፡፡

 1. የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በረጅም ዘመን ታሪኳ ውስጥ ለምዕመናን እምነትና ስርዓት የጠበቀ አገልግሎት እንድትሰጥ ከትውልድ ትውልድ ቀጣይ እንድትሆን ጉልህ ሚና ከተጫወቱት መካከል የሊቃውንት መፍለቂያ የሆኑት የአብነት ትምህርት ቤቶች ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው:: ምንም እንኳን ዘመናት በተቀያየሩ ቁጥር የአብነት ትምህርት ቤቶች ቁጥርና የሚሰጡት የትምህርት ዓይነት በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች እንዲሁም ሀገር አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እየቀነሰ ቢመጣም ዛሬም በተለያየ ቦታ የጥንቱን ትውፊትና ስርዓት ጠብቀው ትምህርቱ ከሚሰጥባቸው ቦታዎች በጥንታዊነቱ እና ቀዳሚነቱ አንዱ የሆነዉ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ ነገር ግን ጉባኤ ቤቱ በሙሉ ተተኪ የቤተ ክርስቲያን አገልጋጦችን የጥንት ሥርዐቱን ሳይለቅና ዘመኑን በዋጀ መሊኩ ለማፍራት እንዲቻል በትምሀርት ቤቱ የሚስተዋሉ መሰናክሎችን መቀነስ ብሎም ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡ በዋናነትም የማደሪያ ቤት፣ የጉባኤ ቤት (የመማሪያ ቤት)፣ የማብሰያ፣ የቤተ መጻሕፍትና የመማሪያ መጻሕፍት፣ የመጸዳጃ፣ የቀለብና የንጹሕ ውኃ፣ የት/ቤቱ ችግሮች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በአብነት ትምህርት ቤቱ ባሉት ችግሮች ምክንያት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ቢገኝም ይህ ችግር ተቋቁመው እየተማሩ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በወቅቱ ዘለቄታዊ መፍትሄ ካልተሰጠው በቀጣይ የተማሪዎች ቁጥርና የትምህርት ቤቱን ህልውና ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ ስለሆነም የትምህርት ቤቱ መጠናከር በአጠቃላይ ለቤተክርስቲያን የሚሰጠውን ጠቀሜታ ግምት ውስጥ በማስገባት እና ከትምህርት ቤቱ ተምረው የሚወጡ ተማሪዎች በሀገራችን በሚገኙ አድባራትና ገዳማት አገልግሎቱ ቀጣይነት እንዲኖረዉ ወሳኝ በመሆኑ ይህን ፕሮጀክት መቅረፅ አስፈላጊ ይሆናል::

 1. የፕሮጀክቱ ግብና ዓላማ

የፕሮጀክቱ ግብ ዘመኑን የዋጁ ተተኪ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትን በማፍራት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማዎች

 • በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለ40 ሐዲሳት እና ፍትሐ ነገስት ተማሪዎች የማደሪያ ቤት ፣ የመማሪያ ቤት እና ቤተመጽሐፍ ግንባታ በማካሄድ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፡፡
 • ሥልጠናና የአሰራር ስርዓት ማዘመን
  1. የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች

በዚህ ፕሮጀክት የአብነት ተማሪዎች እና መምህራን ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ ምእመናን እና ገዳሙ ደግሞ ቀጥተኛ ያልሆኑ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ::

 1. ፕሮጀክቱ ይዘት

በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የሚተገበረዉ የአብነት ት/ቤት ፕሮጀክት በዋናነት ግንባታ፣ስልጠና የአሰራር ስርዓት ማዘመን ያካትታል፡፡

. የማደሪያ ቤት ግንባታ

የማደሪያ ቤቱ ለ40 መጻሕፍት ተማሪዎች ማደሪያ ታስቦ የሚሠራ ሲሆን ፤እያንዳንዱ ክፍል ስፋቱ 4ሜ በ 5ሜ (20 ካሬ ሜትር) የሆነ እና 5 ክፍሎች ያለዉ እያንዳንዱ ክፍል 8 ተማሪዎች የሚይዝ እና አጠቃላይ 40 ተማሪ የሚይዝ ማደሪያ ቤት ይሠራል፡፡ በእያንዳንዱ ክፍሎች 4 ተደራራቢ አልጋ፣ 2 የልብስ ሎከር፣ 1 ጠረጴዛ እና 2 ወንበሮች ይኖሩታል፡፡

. የጉባኤ ቤት እና ቤተ መጽሐፍ ግንባታ       

የመጽሐፍ ቤቱ ከጉባኤ ቤቱ ጋር ተያይዞ የሚሰራ ሆኖ በመካከል ግድግዳ ተሰርቶለት በዉስጥ ክፍል የሚለያይ ይሆናል፡፡ የጉባኤ ቤቱና ቤተ መጽሐፉ ለሐዲሳት እና ፍትሐ ነገስት ተማሪዎች ማስተማሪያ ታስቦ የሚሠራ ሲሆን ስፋታቸዉ እኩል ሆኖ የሁለቱም አጠቃላይ ስፋት 175.2 ካሬ ሜትር ስፋት ያለዉ ቤት የሚገነባ ይሆናል፡፡ የጉባኤ ቤቱና መፅሐፍት ቤቱ በአንድ ጊዜ ከ40 በላይ ተማሪዎችን የሚያስተናግድ አራት መዓዘን የሆነ ሁለት ክፍል ይሰራል፡፡ ጉባኤ ቤት ከመማሪያነት በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት የማኅበር ፀሎት እና የጽዋ መርሐ ግብር አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

. የቁሳቁሶች ግዥ

ለአብነት ትምህርት ቤቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ማለትም ጠረጴዛ ፤የመምህሩ ወንበር እና የአብነት ተማሪዎች የሚቀመጡበት ድጋፍ አግዳሚ ወንበር ይገዛሉ፡፡ ለመምህራን ማረፊያ ቤት አንድ 1.20ሜX0.70ሜ የሆነ ጠረጴዛና አንድ ወንበር ይኖረዋል፡፡

. ሥልጠና  መስጠት

ለአብነት ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ፣ መምህራን እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም ኮሚቴዎች የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ እና አብነት ትምህርት ቤቱን ለማጠናከር የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማድረግ የደረጃ አንድና ደረጃ 2 ሥልጠናዎች የሚሰጡ ይሆናል፡፡

 1. የፕሮጀክቱ የወጪ ገንዘብ ምንጭ

የገንዘብ ምንጩም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል፣ከሀገር ውስጥና በውጭ ማእከል የሚገኙ ምእመናንን በማስተባበር የሚተገበር ሲሆን ጠቅላላ ብር 3,500,000 ያስፈልገዋል፡፡

. የፕሮጀክት ወጪ ዓይነት ወጪ (በብር) ምርመራ
1 የግንባታ ወጪ 2,515,590.00
 • የተማሪዎች ማደሪያ ቤት ግንባታ
1,268,115.63
 •  የጉባኤ ቤት እና ቤተ መፅሐፍት ግንባታ
921,451.71
2 የቁሳቁስ ወጪ 483,566.30
 •   የቤተ መጻሕፍ ቁሳቁስ
116,422.45
 • የጉባኤ እና ማደሪያ ቤት ቁሳቁስ (ቋሚ ዕቃ ግዥ)
367,143.85
3 የስልጠና ወጪ 354,268.93
4 የአሰራር ስርዓት ማዘመን ወጪ 146,574.77
ጠቅላላ የፕሮጀክት ወጪ 3,500,000.00

  የፕሮጀክቱ ጊዜ

ፕሮጀክቱ ግንባታ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሥልጠናዎችና ሥርዐቱን ማጠናከር በየጊዜው የሚሰጥ ይሆናል፡፡

 1. የተግባሪው ተቋም መረጃ

ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ከተመሠረተ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ማህበሩ በየጊዜዉ የአገልግሎት አድማሱን ለማስፋት ይረዳዉ ዘንድ በመላ ሀገሪቱ እና በዓለም ዙሪያ መዋቅሩን በመዘርጋት ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ሲሆን በዚህ መሰረት በሀገር ዉስጥ እና በዉጪ ሀገር 52 ማዕከላት 448 ወረዳ/ንዑስ ማዕከላትና 218 ግንኙነት ጣቢያዎች ፣450 ግቢ ጉባዔያት ይዞ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ማኅበሩ ካሉት የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ የቅዱሳት መካናት መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ሲሆን በገዳማት፣ በአድባራትና በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል፡፡ ይህ ክፍል እንደ አንድ የአገልግሎት ዘርፍ ከተቋቋመበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ባሳለፋቸው 18 ዓመታት ውስጥ ከ130 በላይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ የአደረገ ሲሆን የተተገበሩ ፕሮጀክቶችም ቤተ ክርስቲያን ጠተቃሚ አድርጓል፡፡ ለ186 የአብነት ትምህርት ቤት፣ 226 የአብነት ትምህርት ቤት መምህራን፣ 1,716 የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ እና አራት የአብነት ትምህርት ቤት አስተባባሪዎች በየወሩ ድጎማ በማድረግ የአብነት ትምህር ቤቱ ማስተማሩን እንዲቀጥል እያደረገ ሲሆን፤ አዲስ የአብነት ትምህርት ቤቶችንም እያቋቋመ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገዳማት፣ አደባራትንና የአብነት ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ሁኔታ ለምእመናን በሰፊው እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

አብረን እንሥራ ለውጥም እናመጣለን !

በሀገር ውስጥ ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ምዕመናን የሚከተሉትን አካውንቶች መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡  1000003778828
ወጋገን ባንክ ፡  429211/S01/953

 

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50