የርቀት ትምህርት አገልግሎት ማስጀመርያ ፕሮጀክት

የርቀት ትምህርት አገልግሎት ማስጀመርያ ፕሮጀክት

$550 of $51,109 raised

መግቢያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊት ናት፡፡ አስተምህሮዋና መሠረተ እምነቷ ከአማናዊው መምህር ከኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘ በመሆኑ አማናዊትና ርትዕት ናት፡፡ የዚህች ርትዕት ቤተ-ክርስቲያን ዋነኛ አገልግሎቷም ሐዋርያዊ ተልእኮ ነው፡፡ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታ በአካል የተማሩትን የምስራች ቃል በታዘዙትና በተሰጣቸዉ መንፈሳዊ ኃይል በመታገዝ በብዙ መከራ ዉስጥ ሆነዉ በዓለሙ ሁሉ ዞረዉ አስተምረዋል፤ ነፍሳትንም ለክርስቶስ ማርከዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከቤተክርስቲያን ታሪክ በቀጥታ መረዳት እንደሚቻለው ቤተክርስቲያናችን “ወርቃማ ” ተብለው የሚጠሩ ዘመናትን ያሳለፈች ቢሆንም፣ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጊዜያትንም አሳልፋለች፡፡ ይህም የስብከተ ወንጌል/የሐዋርያዊ አገልግሎት ተደራሽነት እጅግ ውሱን እና የተቋረጠ እንድሆን አድርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሚናፍቁ በገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች መድረስ አልተቻለም፡፡ ይህም መናፍቃኑ ቀድመው በመግባት ብዙዎችን ወደ ምንፍቅና እንዲወስዷቸው በር ከፍቶላቸዋል፡፡ብዙ ወገኖች እውነተኛውን የወንጌል ብርሃን ሳይመለከቱ በእግዚአብሔር ቃል ሳይጠኑ፣ በገጠር በጠረፋማው የሀገራችንና በአጠቃላይ የዓለማችን ክፍል ተበትነው ፣ ድኅነትን እንደናፈቁ ፣ በጎውን ነገር ሳያዩ ሞተ ሥጋ ይቀድማቸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላነት

የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃለ ወንጌል ለዓለም እንዲዳረስ ማድረግ የቤተክርስቲያናችን ዋና ዓላማ ነው። ይህንንም ለማድረግ፣ የተለያዩ ዘመኑን የዋጁ እና የቤተክርስቲያናችንን ትምህርት ተደራሽነት የሚያሰፉ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎችን መጠቀም ይኖርብናል። ከነዚህ ዘመኑን ከዋጁ እና የትምህርት ተደራሽነትን ከሚያሰፉ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴውች ዋነኛው ደግሞ የርቀት ትምህርት አገልግሎት እንደሆነ ይታወቃል።

ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳንም የቅድስት ቤ/ክንን ተልዕኮ መደገፍ ዋና ተግባሩ እንደመሆኑ መጠን ይህንን ሥራ በግንባር ቀደምትነት መጀመር እና ማስፋፋት ይገባዋል። ይህንንም በመረዳት ማኅበሩ ጉዳዩን በስልታዊ እቅድ ከማካተት እና የዳሰሳ ጥናት ከማድረግ ጀምሮ አገልግሎቱን በተጠናከረ መልኩ ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። በተደረገው የዳሰሳ ጥናትም፣ በተለያዩ የእውቀትና የመንፈሳዊነት ደረጃ፣ እንዲሁም በተለያዩ የኑሮ ሁኔታ ያሉ ምዕመናን የቤተክርስቲያንን ትምህርት በርቀት የትምህርት ዘዴ ለመማር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል።

ይሁንና፣ እንዲህ አይነት አገልግሎት በጠንካራ መሠረት ላይ ሊመሠረት እና ቀጣይነቱም የተረጋገጠ ሊሆን ይገባዋል። ለዚህም ሲባል፣ ትምህርቱን የሚከታተሉ ምዕመናን አገልግሎቱን ለማስቀጠል በሚያስችል መልኩ መጠነኛ የክፍያ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ የሚደረግ ይሆናል። ነገርግን፣ ይህ አገልግሎት መነሻው ላይ ከፍተኛ ወጪ እንዳለው ይታወቃል። ይህም፣ አገልግሎቱን ለማደራጀት፣ ግብዓቶችን ለማዘጋጀት (ማዘጋጀት፣ ማሳተም፣ ማከፋፈል)፣ ለኢለርኒንግ የትምህርት ዘዴ የሚሆን መሠረተ ልማት ለመዘርጋት፣ የተለያዩ የመረጃ ቋቶችን እና መተግበርያዎችን (Database and Soft wares) ለማዘጋጀት… ወዘተ የሚውል ነው። ይህም ሁኔታ አገልግሎቱን የማስጀመሩን ሁኔታ ውስብስብ እና ከባድ ስለሚያደርገው ይህን ፕሮጀክት መቅረጽ አስፈላጊ ሆኗል።

የፕሮጀክቱ ዓላማ

የርቀት ትምህርት ዘዴን በመጠቀም የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃለ ወንጌል ለዓለም ሁሉ እንዲዳረስ ማድረግ።

ዝርዝር ዓላማ

 • በመሠረታዊ እና በአጠቃላይ የርቀት ትምህርት መርሐግብሮች ላሉ ኮርሶች የትምህርት ግብዓቶችን ማዘጋጀት።
 • መሠረታዊ የርቀት ትምህርት መርሐግብርን፣ መደበኛ የርቅት ትምህርት ዘዴን እና የኢለርኒንግ የትምህርት ዘዴን በመጠቀም ለ 2000 ምዕመናን ተደራሽ ማድረግ።
 • አጠቃላይ የርቀት ትምህርት መርሐግብርን፣ መደበኛ የርቅት ትምህርት ዘዴን እና የኢለርኒንግ የትምህርት ዘዴን በመጠቀም ለ 1500 ምዕመናን ተደራሽ ማድረግ።
 • በመሠረታዊ ትምህርት መርሐግብር ላሉ ኮርሶች ለያንዳንዳቸው 2000 ሞጁሎች ማሳተም።
 • በአጠቃላይ ትምህርት መርሐግብር ላሉ ኮርሶች ለያንዳንዳቸው 1500 ሞጁሎች ማሳተም።
 • የኢለርኒንግ መሠረተ ልማት ማበልጸግ።

የተማሪዎች መረጃ አያያዝን የሚያቀላጥፍ መተግበርያ ማዘጋጀት።

የፕሮጀክቱ ዝርዝር ተግባራት

 • በአህጉረ በጎሳ መሪዎች/የሀገር ሽማግሌዎች የሚተዳደሩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን መለየት
 • የጎሳ መሪዎችን መምረጥ
 • ለጎሳ መሪዎች ጥሪ ማቅረብ
 • አሰልጣኞችን ማዘጋጀት
 • የሥልጠና ማኑዋል ማዘጋጀት
 • የሥልጠና ቦታ ማዘጋጀት
 • የሥልጠና ቁሳቁስ ማሟላት
 • ሥልጠናውን ማከናወን
 • የሥልጠና ሪፖርት ማዘጋጀት
 • ሰልጣኖችን በአገልግሎት ማሰማራት፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

የበጀት እቅድ

ተ.ቁ ዝርዝር ጉዳይ ታሳቢ የተደረገ በጀት
1 የትምህርት ግብዓቶች ማዘጋጀት 95,000.00
2 የርቀት ትምህርት ሞጁሎችን ማሳተም 960,000.00
3 ለዋናው ማዕከልና ለ6 ማዕከላት መደበኛ አገልጋዮች ቅጥር 360,000.00
4 ለዋናው ማዕከልና ለ6 ማዕከላት የሚያስፈልጉ የቁሳቁስ ግብዓቶችን ለማሟላት 432,000.00
5 የኢለርኒንግ መሠረተ ልማት ማበልጸግ 50,000.00
6 ድራዊ የተማሪዎች መረጃ ሥርዓት(Web based Student Information Management System) መተግበርያ ማዘጋጀት 50,000.00
  ድምር 1,947,000.00
7 መጠባበቂያ (5%) 97350.00
አጠቃላይ 2,044,350.00

የሚያስፈልግ በጀት

የዚህ ፕሮጀክት ጠቅላላ 2,044,350.00 ብር ሲሆን የበጀት ምንጩም በጎ አድራጊ ምእመናን፣ ማኅበራትና ሰንበት ት/ቤቶች ይሆናሉ።

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50