በኦሮሚያ ክልል በምእራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ ለተጎዱ ኦርቶዶክሳዊ ወገኖች የመልሶ ማቋቋም

በኦሮሚያ ክልል በምእራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ ለተጎዱ ኦርቶዶክሳዊ ወገኖች የመልሶ ማቋቋም

$1,030 of $9,979 raised

መግቢያ

የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባለፉት ሺ ዘመናት በሀገራችን በኢትዮጽያ መንግስታዊ ሃይማኖት በመሆን በሀገረ መንግስት ግንባታና ህዝብ አስተዳደር ከሚነገራው በላይ ታላቅ አስተዋጽኦ ማድረጓ እሙን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ባለፉት ሃምሳ አመታት በሀገሪቱ በተነሱ ስሁት ፖለቲከኞችና የባእዳን ትርክት በተጠመቁ ጥራዝ ነጠቅ ተከታዮቻቸው በእጅጉ እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ በጠንካራ ምእመኖቿ በመታገዝ ኦርቶዶክሳዊነትን በማስፋፋት በአሁኑ ሰአት  አገልግሎቷን በሃምሳ ሦስት (53) አህጉረ ስብከት (በአገር ውስጥ አርባ አራት (44) እና በውጭ አገር ዘጠኝ (9))፤ ከ40 ሺህ በላይ ገዳማትና አድባራት፣ ከ500 ሺህ ያላነሱ ካህናትን እያስተዳደደረች፤ ከ45 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ምዕመኗን በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ በኢትዮጵያ ካሉት ሌሎች እምነቶች አንጻር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምእመናን የያዘች ስትሆን ወጣቶችን በሰንበት ትምህርት ቤት የተለያዩ ሃይማኖታዊ ትምህርት በማስተማር በሥነ ምግባር እንዲታነጹ በማድረግ፤ በአብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመክፋት፣ በአጥቢያ በሚሰጡ ስብከተ ወንጌል በማስተማር ትውልዱ እግዚአብሔርን እንዲያውቅ፣ እንዲያመልከውና ትዕዛዙን እና ህጉን አውቆ እንዲተገብርና እንዲድን ስታደርግ ቆይታለች። ይሁን እንጂ የቅድስት ቤተክርስቲያን በጎ እድገትና የምእመናን አንድነት በቀንና በለሊት የሚያቃዣቸው የባእዳን ቅጥረኞች፤ የዲያቢሎስ ጉዳይ አስፈጣሚዎች ቅድስት ቤተክርስቲያንን ክፉኛ እየተፈታተኗት ይገኛሉ፡፡ በቅርቡም በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ በነበረው ጥቃት በርካታ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል፤ 197 ምእመና  ሕይወታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ አጥተዋል፣ አምስት ቢሊየን የተገመተ የኦርቶዶክሳውያን ንብረታቸው በቃጠሎ ወድሟል፤የተረፈውም ተዘርፏል፣ በህየወት የተረፉ ምእመናንም ለአካል እና  ለሥነ ልቦናዊ ጉዳትም ተዳርገዋል፡፡

በመሆኑም ማኀበረ ቅዱሳን እንደ አንድ የቤተክርስቲያኒቱ አካል ከበጎአድራጊ ምእመናን እና ከአበላቱ በማስተባበር ለተጎጂ ምእመናን የተቻለውን ጊዚያዊ ድጋፍ ሲያደር ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ችግሩ ዘርፈብዙና በቀላሉ የማይቀፈር ሆኖ በመገኘቱ ደረጃ በደረጃ የሚፈጸም ዘለቄታዊ የማቋሚያ ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህንንም ለመፈጸም ይረዳ ዘንድ ይህ የመነሻ አነስተኛ የፕሮጀክት ሃሳብ ተቀርጿል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ላይ በተዘራው እጅግ አደገኛና በዘረኝነት የተለወሰ የፖለቲካ ዲስኩርስ የተነሳ ምእመናን በለፉት ሃምሳ አመታት በተለየ መልኩ ደግሞ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት እየደረሰ የሚገኘው ድንገተኛ እና እጅግ አሰቃቂ አደጋዎች በምእመናን ላይ ከፍተኛ እንግልትና የኑሮ ምስቅልል አስከትሏል፡፡ ችግሩም ወደ እስከፊ ደረጃ መድረሱን ባለፉት ሁለት አመታት በተከታታይ በደረሱት ዉድመቶች ለማየት ተችሏል፡፡ አጽራረ ቤተክርስቲያኑ በየክልሉ የመንግት መዋቅር ውስጥ ባላቸው ሃላፊነት በመጠቀም ምእመናንን ተስፋ የማስቆረጥና እምነታቸውን እንዲቀይሩ በማስገደድ፤ የስራ እድል ኢንዲያጡ በማድረግ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጫና በማሳደር፤ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመስተጓጐል፤ እንዲሁም ካህናቱና ምእመናኑ ከአከባቢያቸው ተሰደው እንዲወጡ በማድረግ እጅግ የተቀናጀና ዘርፈ ብዙ ጥቃት እያደረሱ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ለችግሩ ዘለቄታዊ መፍትሄ ለመስጠት የተጠናና የተጠናከረ ፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መፍትሄዎች ማፈላላግ የግድ የሚልበት ደረጀ ላይ ተደርሷል፡፡  ችግሮቹም ስር የሰደዱና ደረጃ በደረጃ የሚቀረፉ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ከዚህም ባሻገር

 • መንግስ ለተጎጂ ወገኖች ትኩረት ባለመስጠቱ ተጎጂዎች በቶሎ ወደ ቀድሞ ህይወታቸው መመለስ መቸገራቸው፤
 • አጥፊዎቹ በታቀደው መሰረት ተጎጂዎች ዳግም እንዳያንሰራሩ በሚያደርግ መልኩ የውድመት ስራ የፈጸሙ መሆኑና ተጎጂዎች በቀላሉ ለማገገም መቸገራቸው
 • በአከባቢው የሚኖሩ ከጥቃቱ የተረፉ ምእመናን ለተጎጆዎች መልሶ መቋቋም በቂ ድጋፍ ለማድግ አቅም ማጣት፤
 • በአጠቃላይ እስካሁን ለተጎጂዎች የተደረጉ ድጋፎች ጊዚያዊ እርዳታ ተኮር በመሆናቸው ተጎጂ ምእመናን አሁንም በእንግልት ላይ የሚገኙ መሆኑ እና ለተጨማሪ አደጋ የሚጋለጡበት ሁኔታ መኖሩ፤ ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ ያሳያል፡፡ ለምሳሌ የዚህ ፕሮጀክት ታሳቢ ተጠቃሚዎች በአጠቃለይ ከሃያ የቤተሰብ አባላት በላይ የሚያሰተዳድሩ በሚሊዮን የሚገመት ንብራት የወደመባቸው ቢሆንም ምንም በዘለቄታው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ባመፈጠሩ በየመቃብ ቤቱ ተጠልልው ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም ይህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ይህ አነስተኛ የሙከራ የመልሶ ማቋቋም ፕሮጅከት መቅረጽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የፕሮጅክቱ አዋጭነት

ፕሮጀክቱ በዋናናት በተጎጂዎች የቀደመ የንግድ ክህሎት እና ልምድ ላይ ተመስሩቶ የተሰነደ ሲሆን፤ የጥፋቱ ሰለባዎች ህይወታቸውን በተለያ የንግድ ስራዎች ላይ ተሰማርተው ይመሩ እንደነበረ ተረጋግጣል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሻሸመኔ ከተማ ከፉተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሤ የሚካሄድበት ፤ የበርካታ የደቡብና የደቡብ ምእራብ የዞንና የወረዳ ከተማዎች መገናኛ መስቀለኛ ከተማ በመሆኑ ጥሩ የንግድ ስራ ገቢ የሚገኝበት ከተማ ናት፡፡ በመሆኑም የተጎጂዎችን የቀደመ የስራ ልምድ እና የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ፕሮጀክቱ ቢተገበር አዋጪ ይሆናል ወይም ተጎጂዎችን በተገቢው መንገድ አትራፊ ደርጋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

የጥፋት ሰለባ የሆኑ ኦርቶዶከሳዊያን ክርስቲያኖች አስፈላጊው የመልሶ መቋቋም ድጋፍ ተደርጎላቸው፣ ወደ ቀደመ የኑሮ ዘይቢያቸው እንዲመለሱና ተረጋግተው እነዲኖሩ ማሰቻል

ዝርዝር ዓላማ

 • ቤትና ንብረት ለወደመባቸው እና የንግድ መተዳደሪያቸውን ላጡ ተጎጂዎች የወደመባቸውን የገቢ ማስገኛ ስራ ለመጀመር የሚችሉበትን ድጋፍ ማድረግ
 • ከዚህ ትግበራ የተገኙ በጎ ውጤቶችና ተግዳሮቶችን በመመዘን ለቀጠዩ ፕሮጀክት የተሻለ የፕሮጀክት ትግበራ ስልት መቀየስ ናቸው።

የፕሮጀክቱ መተግበሪያ ስልት

ይህ ፕሮጀክት ሊተገበር ከታሰበው የመልሶ ማቋቋም ፕሮጅክት አንጻር አነስተኛ እና የሙከራ ፕሮጅክት ነው፡፡ በመሆኑም ፕሮጀክቱ ለተጎጂዎች የቀጥታ የመቋቋሚያ ድጋፍ በማድረግ የሚተገበር ይሆናል፡፡ ፕሮጅክቱ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለእያዳንዱ ተጎጂ መጠነኛ የስራ ማንቀሳቀሻ ወይም ማስጀመሪያ ወጪዎችን ብቻ የሚሸፍን ይሆናል፡፡

ዋና ዋና ተግባራት

 • ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ወይም ከተጎጂዎች ጋር ስለሚደረገው ድጋፍ በዝርዝር መወያየት
 • የወደመውን የንግድ እነቅስቃሴ ሊተካ የሚችለውን የንግድ/ ቢዝነስ አማራጭ መለየት
 • ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን/ግብአቶችን በአይነትና በገንዘብ ማበርከት
 • ተጎጂዎች በታሰበው መልኩ መንቀሳቀሳቸውን መከታተል፤ማበረታታት
 • የማጠናከሪያ የስነልቦና ድጋፍ ማድረግ
 • ተሞክሮዎችን መቀመር ናቸው፡፡

የፕሮጅክቱ ዉጤት

ተጎጂዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀደመ የኑሮ ዘይቢያቸው ተመልሰው እና ተረጋግተው መኖር መጀመራቸው የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ውጤት ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል፡፡ በፕሮጅክቱም አራት ተጎጂ ምእመናን ተጠቃሚ የሚሆኑ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክት ትግበራ ቦታ

የፕሮጅክቱ የትግበራ ቦታ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር በምእራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ ይሆናል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ሁኔታ ተጆጂ ከሆኑት መካካል ለተማረጡ አራት ተጎጂ ምእመናን የሚውል ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች

የፕሮጅክቱ ተጠቃሚዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር በምእራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ሁኔታ ተጆጂ ከሆኑት መካካል ለተማረጡ አራት ተጎጂ ምእመናን ይሆናሉ፡፡

አጋዥ እና ተባባሪ አካላት

ፕሮጀክቱ በአጠቃላ በማእከላት እና ወረዳ ማእከላት፤ ሀገረ ስብከት፤እንዲሁም በበጎ አድራ ምእመናን ድጋፍና ትብብር የሚተገበር ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ስጋት

ተጎጂዎች በአዲስ መልክ ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ነገሮች በፉጥነት ለመስተካከል ካልቻሉ ሊገጥማቸው የሚችል የስነልቦና ጫና መፈጠሩና ምእመናን ወደ ቀቢጸ ተስፋ ሊያመሩ ወይም የመሰደድ እጣፈንታ ሊደርስባቸው መቻሉ ዋነኛው ስጋት ሲሆን ፖለቲካዊ ግርሻቱ የሚፈጥረው ችግርም የሚጀምሩትን ንግድ በቀላሉ እንዳያድግ ሊደርገው ይችላል፡፡ ስለሆነም ማኀበሩ ከሎሎች ስራዎች ጎን ለጎን የስነልቦናና ትክኒካዊ የሙያ ድጋፍ በማድረግ ችግሩን ለመቋቋም የሚሰራ ይሆናል፡፡

ክትትልና ድጋፍ

ፕሮጅክቱ በሚተገበርበት እና ከትግበራውም በኃላ በማኅበሩ የክትትልና ምዘና ባለሞያዎች የፕሮጅክቱን አጠቃለይ ሂደት፤የተገኘውን ውጤት፡ የተጠቃሚዎችን የለውጥ ሁኔታና መሰል ጉዳዮችን የመከታታልና የድጋፍ ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የክክትትልና ምዘና ሪፖርትም ለሚመለከታቸው አካላት በተገቢው ጊዜ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ አስተዳዳር

ፕሮጀክቱ በማኅበረ ቅዱሳን የሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል እና በተዋቀረው የመልሶ ማቋቋም አብይ ኮሚቴ የሚመራ ይሆናል፡፡ እንደስፈላጊነቱም ኮሚቴው ከዋና ክፍሉና ከማኅበሩ  ጽ/ቤት በሚሰጠው አቅጣጫ ፕሮጅቱን የሚፈጽም ይሆናል፡፡

የፕሮጅክቱ የጊዜ ሠሌዳ

የፕሮጅክቱ ታሳቢ ተጠቃሚዎች የሚገኙበት ሁኔታ እጅግ አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልግ ከመሆኑ አንጻር ፕሮጅክቱ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ የሚተገበር ይሆናል፡፡

የፕሮጅክቱ አጠቃላይ ወጪ

 ብር 349,277.50

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50