ይለግሡ -አዳዲስ አማንያንን ለማጥመቅና ለማጽናት የሚደረጉ ጉባኤያት ፕሮጀክት

አዳዲስ አማንያንን ለማጥመቅና ለማጽናት የሚደረጉ ጉባኤያት ፕሮጀክት

$9,385 of $15,708 raised

          “ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።ዳን 12÷3

 

መግቢያ

ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ከተመሠረተበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያናችን ከተባባሪ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ከእነዚህም አገልግሎቶች መካከል ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ከቤተ ክርስቲያን የኮበለሉትን ማስመለስ፣ አዳዲስ አማንያንን አስተምሮ ማስጠመቅ፣ ያመኑትን ማጽናት ይገኝበታል፡፡በዚህም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለፉት ዓመታት  በተከናወነው የሐዋርያዊ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች 250 ሺህ በላይ አዳዲስ አማንያንን ለማስጠመቅ ተችሏል፡፡

ይህንን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አጠናክሮ በመቀጠል ብዙዎችን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን አባላት ለማድረግ፣ የጠፉትን ለመመለስና ምእመናንን በምግባር በሃይማኖት የሁሉንም ድጋፍና አስተዋጽኦ ይጠይቃል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን  የሐዋርያዊና የስብከተ ወንጌል አገልገሎቷን ተደራሽ ለማድረግ ከዚህ በታች በተቀረጸው ፕሮጀክት የተቻለዎትን ድጋፍ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ስም ይጠየቃሉ።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ በ12 አኅጉረ ስብከት በተመረጡት አዳዲስ አማኞች በስፋት ሊገኙባቸው በሚችሉ የወረዳ አጥቢያዎች/መካነ ስብከት መምህራንና መዘምራንን በመላክ ለ3 ቀናት ስብከተ ወንጌልና በማድረስ ያላመኑ እንዲያምኑ፣ በተለያየ ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን የሄዱ እንዲመለሱና ኦርቶዶክሳዊያኑ በሃይማኖትና በምግባር እንዲጸኑ የሚያግዙ 100 ጉባኤያትን ማከናወን ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የሚፈጸምባቸው አካባቢዎች

ማኅበረ ቅዱሳን የሐዋርያዊ አገልግሎቱን በስፋት እየተፈጸመባቸው እና ብዙ አዳዲስ አማንን ያሉባቸው አካባቢዎች (የመተከል ሀገረ ስብከት፣ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት፣ የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት፣ የቤንች ማጅ ሀገረ ስብከት፣ የከፋና ሸካ ሀገረ ስብከት፣ የወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት፣ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀገረ ስብከት) በዋናነት ይገኙበታል፡፡

የፕሮጀክቱ በጀት

አዳዲስ አማንያንን ለማስጠመቅና በምግባር በሃይማኖት ለማጽናት የሚያግዙ ጉባኤያት ለአንድ ጉባኤ ወጪ 5,000.00 ብር ሲሆን አጠቃላይ የዚህ ፕሮጀክት ወጪ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ነው፡፡

ለሀገር ውስጥ ድጋፍ አድራጊዎች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000195489541፣

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50