የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ ሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና

የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ ሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና

$1,520 of $75,000 raised

 

መግቢያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊት ናት፡፡ አስተምህሮዋና መሠረተ እምነቷ ከአማናዊው መምህር ከኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘ በመሆኑ አማናዊትና ርትዕት ናት፡፡ የዚህች ርትዕት ቤተ-ክርስቲያን ዋነኛ አገልግሎቷም ሐዋርያዊ ተልእኮ ነው፡፡ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታ በአካል የተማሩትን የምስራች ቃል በታዘዙትና በተሰጣቸዉ መንፈሳዊ ኃይል በመታገዝ በብዙ መከራ ዉስጥ ሆነዉ በዓለሙ ሁሉ ዞረዉ አስተምረዋል፤ ነፍሳትንም ለክርስቶስ ማርከዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከቤተክርስቲያን ታሪክ በቀጥታ መረዳት እንደሚቻለው ቤተክርስቲያናችን “ወርቃማ ” ተብለው የሚጠሩ ዘመናትን ያሳለፈች ቢሆንም፣ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጊዜያትንም አሳልፋለች፡፡ ይህም የስብከተ ወንጌል/የሐዋርያዊ አገልግሎት ተደራሽነት እጅግ ውሱን እና የተቋረጠ እንድሆን አድርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሚናፍቁ በገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች መድረስ አልተቻለም፡፡ ይህም መናፍቃኑ ቀድመው በመግባት ብዙዎችን ወደ ምንፍቅና እንዲወስዷቸው በር ከፍቶላቸዋል፡፡ብዙ ወገኖች እውነተኛውን የወንጌል ብርሃን ሳይመለከቱ በእግዚአብሔር ቃል ሳይጠኑ፣ በገጠር በጠረፋማው የሀገራችንና በአጠቃላይ የዓለማችን ክፍል ተበትነው ፣ ድኅነትን እንደናፈቁ ፣ በጎውን ነገር ሳያዩ ሞተ ሥጋ ይቀድማቸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላነት

የሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት በተለያዩ አህረ ስብከት ከሰባክያነ ወንጌል እጥረት የተነሳ ስብከተ ወንጌል ያልተዳረሰባቸው እና በመናፍቃን የተወረሩ አካባቢዎች በመኖራቸው ከየማኅበረሰቡ መካከል ሰባኬ ወንጌል ሊሆኑ የሚችሉ ወጣቶችን መልምሎ በማሰልጠን ስብከተ ወንጌልን ተደራሽ በማድረግ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ የሆኑትን አስተምሮ ማሳመንና ማስጠመቅ፣ በተለያየ ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን የወጡትን አስተምሮ ለመመለስ እና አምነው የተጠመቁትን በምግባር በሃይማኖት ማጽናት ያስፈልጋል፡፡

  • በአህጉረ ስብከቶቹ ያለውን የሰባክያነ ወንጌል እጥረት ችግር በመቅረፍ ቅዱስ ወንጌል ተደራሽ ለማድረግ ይረዳል፡፡
  • የመምህራኑን አቅም የሚያጎለብትና ለተሻለ አገልግሎት የሚያበቃ ይሆናል፡፡
  • በአካባቢው ለሚኖሩና አዲስ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት በማስተማር ምእመናኑ በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ያደርጋቸዋል፡፡
  • የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ላልደረሳቸው ወገኖች የቤተክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት በማስተማር አሳምኖ ለማስጠመቅ ይረዳል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

በተለያዩ  ገጠራማና ጠረፋማ አካባቢዎች የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ አዳዲስ አማንያንን ለማስተማርና ለማስጠመቅ፣ ምእመናንን በምግባር በሃይማኖት ለማጽናትና የጠፉትን ለመመለስ የሚያገልግሉ 1000 ሰባክያነ ወንጌል ማሰልጠን

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ

  • ለ1000 አዳዲስ ሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና ብር 3,000,000.00
  • ለአንድ ሰባኬ ወንጌል ሥልጠና አማካይ ወጪ ብር 300

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50