የመቐለ ደብረ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች ማደሪያ ቤት ግንባታ

የመቐለ ደብረ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች ማደሪያ ቤት ግንባታ

$650 of $91,839 raised

መግቢያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 49 አህጉረ ስብከት ያላት ሲሆን፤ በማህበረ ቅዱሳን ቅ/መ/መ/ት/ቤቶች/አ/ማስ በ2003 እና 2004 ዓ.ም. በተሰበሰበዉ መረጃ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከ2348 በላይ የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዳሉ የታወቀ ሲሆን ከእዚህ መካከልም የመቀሌ ደብረ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ አብነት ትምህርት ቤት አንዱ ነው፡፡
በእዚህ የአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ 202 ተማሪዎች ሲገኝ 52 የሳር ጎጆዎች አሉ፡፡ በአንድ ጎጆ ከ4-5 ተማሪዎቹ ይኖራሉ ይህም በመሆኑ ተማሪዎች ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ ከሆን በተጨማሪ ዝናብ ሲዘንብ ስለሚያፈስ የሚማሩባቸዉ መፅሐፍት እየተበለሹ ከፍተኛ ችግር ዉስጥ ይገኛሉ፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍ ማኅበረ ቅዱሳን 3,499,501.74 ብር የሚያወጣ ማደሪያ ቤት ምዕመናንን በማስተባበር ለመግንባት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት
የመቀሌ ደብረ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤት ብዙ ሊቃውንትን ያፈራ እያፈራ የሚገኝ የአብነት ትምህርት ቤት ቢሆንም በአብነት ትምህርት ቤቱ ውስጥ ባሉት ችግሮች ማለትም የጉባኤ ቤት፤የማደሪያ ቤት፤የማብሰያ እና መፀዳጃ ቤት ባለመኖር ምክንያት በትምህርት ሥርአቱ ላይ በከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የማደሪያ ቤት መገንባት ያስፈለገበት


• የአብነት ትምህርት ቤቱን ህልውና ለመጠበቅ፤
• የተማሪዎችን ቁጥር እንዳይቀንስ ለማድረግ፤
• የተማሪዎችን የትምህርት ጊዜ ቆይታ ለማሳጠር እና ቤተክርስቲያን የሚያገለግሉ ሊቃዉንት በብዛት ለማፍራት ይህን ፕሮጀክት መቅረፅ አስፈላጊ ሆኗል።
የፕሮጀክቱ ግብ እና ዓላማ
የፕሮጀክቱ ግብ
• ዘመኑን የዋጁ የቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንትን በማፍራት የቤተክርስቲያን አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ::
የፕሮጀክቱ ዓላማ
ለ48 የድጓ እና ለ48 የቅኔ ተማሪዎች 2 ብሎክ የማደሪያ ቤት ይገነባል፡፡
የአብነት ትምህርት ቤት የአሰራር ስርዓት ማዘመን፡፡
የፕሮጀክቱ ይዘት
በመቀሌ ደብረ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የሚተገበረዉ የአብነት ትምህርት ቤት በዋነኛነት
• ግንባታ፡- አንድ ብሎክ 6 ክፍሎች ያሉት ለ48 የድጓ ተማሪዎች እና አንድ ብሎክ 6 ክፍሎች ያሉት ለ48 የቅኔ ተማሪዎች በግቢ ተለይቶ የማደሪያ ቤት ይገነባል፡፡
• የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፡- ከተማሪ ቅበላ እስከ ስምሪት ያለዉን አሰራር ያጠቃልላል፡፡
የማደሪያ ቤት ግንባታ
የማደሪያ ቤቱ ለ96 ተማሪዎች ማደሪያ ታስቦ 12 ክፍሎች የሚሰራ ሲሆን እያንዳንዱ ክፍል 20 ካሬ ሜትር ስፋት ሲኖረዉ 8 ተማሪዎች የሚይዝ ይሆናል፡፡ በእያንዳንዱ ክፍሎች 4 ተደራራቢ አልጋ፣ 2 የልብስ ሎከር፣ 1 ጠረጴዛ እና 2 ወንበሮች ይኖሩታል፡፡
የፕሮጀክቱ የትግበራ ቆይታ ጊዜ፡- 1 ዓመት፤
የፕሮጀክቱ ወጪ
የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ ብር 3,499,501.74

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50