የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ተቋም ፕሮጀክት

የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ተቋም ፕሮጀክት

$0 of $64,152 raised

የፕሮጀክቱ መጠሪያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ተቋም ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ ግብ

የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ተቋምን ማጠናከር

የፕሮጀክቱ ዓላማ

 • የብሮድካስት አገልግሎት ተቋም አገልግሎተን ማጠናከር እና ማስፋፋት
 • ምእመናን የብሮድካስት አገልግሎትን በገንዘብ ፣በቁሳቁስ በመደገፍና አገልግሎቱ እንዲቀጥል ማድረግ
 • አገልገሎቱን ሊያግዙ የሚችሉ የፕሮዳክሽን ዕቃዎችን መግዘት
 • የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የስብከተ ወንጌል ተደራሽነቱን ማስፋፋት

የፕሮጀክቱ ይዘት

ማኅበረ ቅዱሳንም የወንጌል አገልግሎትን ላለፉት 7 ዓመታት በቴሌቭዥን teleministry/ televangelism እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲያስተላለፍ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል። በመጀመርያ  ኢቢየስ EBS ከየካቲት ወር 2005 ዓ/ም ጀምሮ  እስከ ህዳር 2008 ዓ/ም ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮችን በሳምንት ለ30ደቂቃ ሲያስተላልፍ የነበረ ሲሆን፤ በአንዳንድ ምክንቶች  ከኢቢየስ የነበረን ስምምነት ቢቋረጥም፤  በ11 የውጭ አገራት  ኢንተርኔት መርሐ ግብር የቀደመ ይዘቱን ሳይለቅ እየተላለፈ ይገኝ ነበር ፡፡በተጨማሪም ከየካቲት ወር 2007 ዓ/ም ጀምሮ የአገልግሎት አድማሱን ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ በ ኦን ላየን ኢንተርኔት ቴሌቭዥን መርሐ ግበር ያስተላልፍ ነበር፡፡ እንዲሁም ከኢብየስ መቋረጥ በኃላ በ2008ዓ/ም በኦሮምኛው የቋንቋ ዘርፍ በኦቢየስ/OBS ባገኘነው የአየር ሰዓት  እድል በመጠቀመም በሳምንት ለ30ደቂቃ ለአንድ ዓመት ያህል መንፈሳዊ ዝግጅቶችን ሲያስተላለፍ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ማኅበሩ ይህን ክፍል ባቋቋመ በአጭር ጊዜያት ውስጥ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚጠቅሙ በርካታ ሥራዋችን ሠርቷል፣ ለብዙ ነፍሳትም የመዳን ምክንያት ሆኗል፣ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምንነት ያልተረዱ ሰዎችም ማኅበሩን በግልጽ እንዲያውቁ አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ ከመስከረም 2010 ዓ/ም ጀምሮ የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ተቋም እንደ አዲስ በመቋቋም በአሌፍ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሳምንት ለ14 ሰዓታት በመከራየት መርሐ ግብሩን  በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣በትግሪኛ ቋንቋዎች ወንጌልን ለማድረስ በስፋት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በመጨረሻም በአሌፍ ቴሌቭዥን ሲያስተላለፍ የቆየውን የሁለት ዓመት የቴሌቭዥን ስርጭት እንደ ትልቅ ልምድ እና ግብዓት በመውሰድ፤ የማኅበረ ቅዱሳን የሚድያ አገልግሎት ተፈላጊነት ከምን ጊዜውም በላይ እየጨመረ በመምጣቱና  ዘመን አፈራሹን ሚድያም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከምንጊዜውም በላይ መጠቀም ያለባት በመሆኑ  ምክንያቱም ሚድያ በዘመናችን አራተኛ መንግስት ስለሆነ ይህንን በመረዳት፤ ከመስከረም 1/2012 ዓ.ም ጀምሮ ማኅበሩ (የገል) የራሱን ቴሌቭዥን ጣቢያ ከፍቶ የ24 ሰዓታት የሙከራ ስርጭቱን ጀምሯል። የብሮድካስት ሚዲያውንም አቀራረብ በማዘመን ለሁሉም ተደራሽ ለመሆን ጥረት እያደረገ ይገኛል። በይበልጥ አሁን የጀመረው የቴሌቭዥንና ሬዲዮ የ24 የሙከራ ስርጭት በራሱ በብዙ መልኩ ከምእመናን ጋር ቤተሰብ ለመሆን እያስቻለው ይገኛል። ምእመናን በሚመቻቸው ሰዓት ማየት እንዲችሉ ምቹ ሁናቴን  ፈጥሯል።

ሆኖም አገልግሎቱ ከበቂ የሰለጠነ የሰው ኃይልና ከፍተኛ በጀት በተጨማሪ የተለያዩ የፕሮዳክሽን ዕቃዎች የሚያስፈለጉት ስለሆን ከዚህ በታች አገልግሎቱን ለማፋጠን የሚረዱንን በዝርዝር አስቀምጠናል፡፡

በአጠቃላይ ይህ ፕሮጀክት ምእመናን/ደጋፊ አካላት አግልግሎቱን እንዴት እና በምን መደገፍ እንደሚቸሉ በግልጽ የሚያሳይ ነው በዚህም መሠረት ደጋፊ አካላት በተመቻቸው እና በፈለጉት አማራጭ ፕሮክቱን መደገፍ ይችላሉ፡፡

ለፕሮጀክቱ የሚፈለጉ ዓይነት በዝርዝር

 • ቪድዮ ካሜራ፡-
  • Sony pxw-Z280 4K 3-CMOS ½” Sensor XDCAM Camcorder : የአንዱ ዋጋ 378,350.00 የሚፈለገው ብዛት ሁለት (756,700.00)
  •  Canon XF405 4K UHD 60P Camcorder with Dual-pixel Autofocus : የአንዱ ዋጋ 241,500.00 የሚፈለገው ብዛት ሁለት (483,000.00)
 • ካሜራ ትራይፖድ፡-
  •  Manfrotoo 526,545BK Professional Video Tripod System with 526 Head : ዋጋ 55,200.00
  •  Manfrotoo MVH500A Fluid Drag Video Head with MVT502AM Tripod and Carry Bag : ዋጋ 40,200.00
  • Libec LX7 M Tripod With Pan and Tilt Head and Mid-Level  :  ዋጋ 37,950.00
  • Manfrotto MVMXPRO500US XPRO Aluminum Video Monop  :  ዋጋ 32,200.00
 • የካሜራ ቪድዮ መብራት፡-
  • Godox LED-1000W White Light Version 70W Dimple Video   Light panel with Remote Control : ዋጋ 37,950.00 የሚፈለገው ብዛት አምስት (189,150.00)
 • ኒክ ማይክ ዋይርለስ፡-
  •  Sony uwp-D11 integrated Digital wireless Bodypack Lavalier Microphone System :  የአንዱ ዋጋ 28,750.00 የሚፈለገው ብዛት አምስት(143,750.00)
  •  Sony uwp-D12 integrated Digital wireless Handheld Microphone ENG System 823-865mhz : ዋጋ 28,750.00 የሚፈለገው ብዛት ሁለት (57,500.00)

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ

አንድ ሚልየን ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር (1,796,250.00)

የፕሮጀክቱ የትግበራ ቆይታ ጊዜ

ለአንድ ዓመት (12 ወራት)

$
 
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50 One Time