በሐላባ ፣ ከምባታ ጠምባሮ ሀገረ ስብከት የሐዋርያዊ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረጊያ ፕሮጀክት

የሐላባ፣ ከምባታ ጠምባሮ ሀገረ ስብከት የሐዋርያዊ አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት

$1,190 of $189,350 raised

መግቢያ

የሐላባ፣ከምባታ ጠምባሮ ሀገረ ስብከት መገኛ በደቡብ ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዱ በሆነው በከምባታ ጠምባሮ ዞን ሲሆን በሰሜን በኩል ጉራጌ፣ በደቡብ ምሥራቅ በኩል ሐዲያ፣ በደቡብ በኩል ወላይታ፣ በደቡብ ምዕራብ በኩል ዳውሮ፣ በሰሜን ምዕራብ በኩል ሐዲያ እና በምስራቅ በኩል አላባ ልዩ ወረዳ ያዋስኑታል፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ዱራሜ ሲሆን ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ 300 ኪ.ሜ አካባቢ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 1,355.89, ካሬ ኪ.ሜ ሲሆን በ1999 ዓ/ም በተደረገው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት የዞኑ ጠቅላላ ነዋሪ ሕዝብ ብዛት 1,080,837 ሲሆን ከጠቅላላ ሕዝብ መካከል 6.55% ብቻ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እምነት ተከታይ ናቸው፡፡

ይህ የሚያመለክተው በአካባቢው ያለው የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት ውሱንነት ያለበትና የአጽራረ ቤተክርስቲያን በተለይም የፕሮቴስታንትዚም እንቅስቃሴና ተጽዕኖ  በከፍተኛ ደረጃ የሚታይበት መሆኑን ነው። በዚህም ምክንያት የሥላሴን ልጅነት ሳያገኙ የሚኖሩ፣ ከቤተ ክርስቲያን የኮበለሉ߹ በስብከተ ወንጌል ተደራሽ ያልሆኑና የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረተ እምነት የሚያስተምራቸው በማጣታቸው በክህደት ትምህርት ተውጠው የቀሩ በርካቶች ናቸው፡፡

በሀገረ ስብከቱ ያለው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተግዳሮት

    የአብያተ ክርስቲያናትና አገልጋይ ካህናት አለመኖር

 • በብዙ አካባቢዎች የኪዳን ፣ የቅዳሴ አገልግሎት፣የሙታን ፍትሐት፣ የልጆች የ40/80 ቀናት የልጅነት ጥምቀት አገልግሎት የለም፡፡ ለምሳሌ፡-

በሀገረ ስብከቱ ከሚገኘው ጠምባሮ ወረዳ 30 አብያተ ክርስቲያናት መካከል

 • አሥራ ዘጠኙ አብያተ ክርስቲያናት ምንም ካህን የሌላቸው ናቸው፡፡
 • በሳምንት የሚቀደስባቸው ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው፡፡
 • አራቱ አብያተ ክርስቲያናት በወር አንድ ጊዜ ይቀደስባቸዋል፡፡
 • ሌሎቹ በዓመት የሚቀደስባቸው ናቸው፤ ይህም ሆኖ አገልጋዮች ሳይገኙ ሲቀሩ በዓመትም የሚታጎልባቸው አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡
 • በአካባቢያቸው አገልጋይ ካህናትና አብያተ ክርስቲያናት ባለመኖራቸው ለቀብር ብዙ ርቀት መጓዝ (ሬሳ እስከሚሸት ድረስ ማቆየት) ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ወደ አብያተ ክርስቲያናት ብዙ ርቀት ሲጓዙ በአውሬ የሚበሉ ሕጻናት አሉ (ለምሳሌ በአንድ ዓመት በአንጋጫ ወረዳ ብቻ 14 ሕጻናት በጅብ ተበልተዋል)፡፡
 • አብያተ ክርስቲያናትም የሌላቸው በርካታ ቀበሌዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በሀገረ ስብከቱ በሚገኘው አንጋጫ ወረዳ ከ22 ቀበሌዎች መካከል 10 ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ይገኛሉ፡፡
 • በካህን እጥረት የተዘጉ፣ አቧራ የወረራቸው አብያተ ክርስቲያናት በርካታ ናቸው፡፡

የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ተደራሽ አለመሆንና አለመጠናከር

 • በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤት የላቸውም፡፡ ለምሳሌ በሀገረ ስብከቱ በሚገኘው ጠምባሮ ወረዳ ከሚገኙ 30 አብያተ ክርስቲያናት መካከል 20 አብያተ ክርስቲያናት የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት የላቸውም፡፡ እንዲሁ አንጋጫ ወረዳ  ከሚገኙት 22 ቀበሌዎች አሥራ ስድስት ቀበሌዎች ሰንበት ት/ቤት የላቸውም፡፡
 • ሰንበት ት/ቤት ያላቸውም አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶቹ በአግባቡ የተደራጁ አይደሉም፤
 • ሕጻናትንና ወጣቶችን ሰብስቦ የሚይዝ የሚያስተምር ሰባኬ ወንጌል የላቸውም፣ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ፣ ቤተ መጻሕፍትም የላቸውም፡፡
 • በሰንበት ት/ቤቶቹም የሚሳተፉ የወጣቶችና ሕጻናት ቁጥራቸው አናሳ ነው፡፡

የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተደራሽነት ውሱንነት ያለበትና የተቋረጠ መሆን

 • ለምእመናን ቅዱስ ወንጌልን ተደራሽ ለማድረግ ጠንካራ የሰርክ ጉባኤ አይደረግም፡፡
 • በሀገረ ስብከቱ ባሉ ወረዳዎች ገጠራማም ሆነ ከተማዎች የሚደረጉ ጉዳይ ተኮር ጉባኤያት የሉም፡፡
 • በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተሰማሩ አገልጋይ ሰባክያነ ወንጌል ቁጥር አናሳ ሲሆን ሰባኬ ወንጌል የሌለባቸው በርካታ አካባቢዎች ይገኛሉ፡፡
 • የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱ በመቋረጡ ምክንያት ምእመናን ከቤተ ክርስቲያን ስለወጡ ምንም ክርስቲያን የሌለባቸው አካባቢዎችና ቀበሌዎች አሉ፡፡

ከፍተኛ የሆነ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን (መናፍቃን) እንቅስቃሴ

 • መናፍቃን በአካባቢው ቀድመው በመግባት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ በርካታ ጉዳት አድርሰዋል፡፡
 • በገጠርም በከተማም ጩኸት የበዛባቸው ትልልቅ ኮንፈረንሶች ይደረጋሉ፡፡
 • ማኅበራዊ አገልግሎት በማስፋፋት ምንፍቅናቸውን ለማስፋፋት ይጠቀሙበታል፤ ምእመናን ላይም ጫና ያደርጋሉ (ከእድርና እቁብ ምእመናንን ያስወጣሉ)፤የእነዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን መናፍቅ መሆን እንዳለባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ምእመናን ላይ ጫና ያሳድራሉ፡፡
 • ሕጻናትና ወጣቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይሄዱ ጫና ያደርጋሉ፡፡
 • በርካታ አዳራሾች በመስራት ምንፍቅናቸውን ያስፋፋሉ፣ በብዙ አካባቢዎች በአማካይ በአንድ ቀበሌ ከ8-14 አዳራሾች ሲኖራቸው፤ ምሳሌ ለመጥቀስ ያክል በጠምባሮ ወረዳ በሚገኙ 24 ቀበሌዎች 117 የመናፍቃን አዳራሾች ይገኛሉ፡፡
 • የአቅመ ደካማ ልጆችን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ በማድረግ በርካታ ልጆችን ከሃይማኖት አስወጥተዋል፡፡
 • የኦርቶዶክሳውያንን ቦታ ይዞታ ይነጥቃሉ፣ የቤተ ክርስቲያንን የልማት ቦታ ያወድማሉ፡፡
 • ከተለያዩ ክፍላት ዓለማት የተሰበሰቡ መናፍቃን በተደጋጋሚ ሁኔታ የኮንፈረንስና የጸሎት መርሐግብር ያደርጋሉ፡፡ (በሄሊኮፕተር ጭምር ሰዎችን በማጓጓዝ ያስተምራሉ) “በ7 ዓመት ከኦርቶዶክስ የጸዳች ዞን እናዳርጋለን” ብለው በይፋ ይናገራሉ፡፡
 • የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም በገበያ ቦታ፣ ቤት ለቤት፣ በሐዘንና በሰርግ ቤት፣ በእረኝነት ቦታ፣ በት/ቤቶችም ጭምር የሐሰት ትምህርታቸውን ያስፋፋሉ፡፡

ከመናፍቃን ቅሰጣ የተረፉት ምእመናን “ድረሱልንና መንግስቱን በጋራ እንውረስ” እያሉ ጥሪያቸውን               ያስተላልፋሉ፡፡ እርስዎም ከታች የተጠቀሱትን የሐዋርያዊ አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በመደገፍ             ክርስቲያናዊ  ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡

የሐዋርያዊ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ዓበይት ተግባራት

ተ.ቁ ፕሮጀክት የአንዱ በጀት ጠቅላላ በጀት
1 100 ሰባክያነ ወንጌል ሥልጠና 4000.00 400,000.00
2 50 ካህናት ሥልጠና 2000.00 100,000.00
3 25 ሰባክያነ ወንጌል ቅጥር 2,000.00 600,000.00
4 50 ጎሳ መሪዎች/ሀገር ሽማግሌዎች ሥልጠና 3000.00 150,000.00
5 20 ጉዳይ ተኮር ጉባኤያት ማከናወን 15,000.00 300,000.00
6 5 የስብከተ ወንጌል ሳምንት 60,000.00 300,000.00
7 በ6 የወረዳ ከተሞች ወርሐዊ ጉባኤያትን  ማጠናከር 24,000.00 144,000.00
8 የ25 ሰንበት ት/ቤቶችን አገልግሎት ማጠናከር 100,000.00 1,000,000.00
9 20 የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ማስከፈት 60,000.00 1,200,000.00
10 2 ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት ግንባታ 1,000,000.00 2,000,000.00
11 የ2 ሞተር ብስክሌት ግዥ 75,000.00 150,000.00
12 የ10 ድምጽ ማጉያ ግዥ 15,000.00 150,000.00
13 ቋንቋዎች የመዝሙርና ስብከት ዝግጅትና ሥርጭት 20,000.00 80,000.00
14  5 የስብከት ኬላ አዳራሽ ግንባታ 200,000.00 1000,000.00
ድምር   7,574,000.00

ማጠቃለያ

የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እኔ እላካለሁ በማለት ለሐዋርያዊ አገልግሎት መትጋት  የእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አካል ድርሻ በመሆኑ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን  በስሑታን ትምህርት ለተወሰዱትና ቃለ እግዚአብሔርን ናፍቀው በሜዳ ለሚቅበዘበዙት ወገኖቻችን እንደርስላቸው ዘንድ “ኑ የወንጌል ማኅበርተኛ እንሁን!” እያለ ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

 

$
Select Payment Method
Personal Info

Credit Card Info
This is a secure SSL encrypted payment.

Donation Total: $50